መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ “ከተመደብኩበት ጨዋታ የምቀየረው ለምንድነው ብዬ ኮሚቴውን ስጠይቅ የተሰጠኝ መለስ አንተ ለውንብድና አትመችም የሚል ነው” አርቢትር ኃይለየሱስ ባዘዘው
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣብቸኛዋ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ

“ከተመደብኩበት ጨዋታ የምቀየረው ለምንድነው ብዬ ኮሚቴውን ስጠይቅ የተሰጠኝ መለስ አንተ ለውንብድና አትመችም የሚል ነው” አርቢትር ኃይለየሱስ ባዘዘው

አጋራ
አጋራ

​በዮሴፍ ከፈለኝ

አቶ ባዘዘው በለጠና ወ/ሮ ስመኘው ታረቀኝ 
በመሰረቱት ትዳር 14 ልጆች ሲወልዱ ኑሮአቸው 
ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 3 በተለምዶ ስቴድየም 
አከባቢ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ቤተሰብ የተገኘው 
እንግዳችን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት 
ሳይንስ መምህር ሲሆን በ2010 በእግር ኳስ 
አሰልጣኝነት የፒ ኤች ዲውን ያገኛል ተብሎ 
ይጠበቃል፡፡ 

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከዲፕሎማ 
3ኛ ዲግሪ ድረስ ሲያገኝ ሙሉ ታሪኩ በዚችው 
ከተማ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ከሰሞኑ የኢትዮጵያ 
እግር ኳስ ፌደሬሽን የዳኞች ኮሚቴ 2009 
የስራ አፈፃፀሙን 87 በመቶ የተሳከካ ነበር 
ማለቱን በመገረም የሰማው ኢንተርሽናል 
አርቢትር ሃይለየሱስ ባዘዘው ከዮሴፍ ከፈለኝ 
ጋር በነበረው ሰፋ ያለ ቆይታ በዳኝነት ዘመኑ 
የገጠመው ፈተና፤ ከዳኞች ኮሚቴ ጋር 
ስለነበረው ሻካራ ግንኙነት፣ ገንዘብ ተኮር ዳኝነት 
እያየው ነው ማለቱ፣ ከኮሚሽነሮች ጋር ስላለው 
ግንኙነት ፣ከተመደበበት ጨዋታ በተደጋጋሚ 
ስለመታገዱ፣ስለተነጠቀው ኢንተርናሽናል ባጅና 
ሌሎች ጉዳዮች ድፍረት የተሞላበት ምላሽ 
ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ፡- ቤተክርስትያን ታዘወትራለህ አክራሪ 
ነህ ማለት ይቻላል?
ሃ/የሱስ፡– በመንፈሳዊ ህይወታችን በርት 
ተን አንድ ፈጣሪን የማንጠይቅ ከሆነ ስራችን 
ሊበላሽ ይችላል፡፡ በግል አስተዳደጌ በተለይ 
የአባቴ ምክር እውነትን አትለፍ የሚል 
ነውና ሰው መውደድና እምነትን እንድማር 
አድርጎኛል፡፡ ቤተክርስትያን መሄድና መፀለይ 
እውነተኛ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ እውነት 
በርግጥ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ያም ቢሆን 
ግን መዳኑም ያለው እውነት ውስጥ በመሆኑ 
አልፈራም፡፡ በተረፈ አምላኬን ለመቅረብ 
ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ፡፡ በስራዬም ትልቅ 
እገዛን አግኝቻለሁ፡፡ 
ሀትሪክ፡- ዳኝነትን እንዴት ጀመርክ በተለይ
ተምሳሌት የሆነህ ሰው አለ?
ሃ/የሱስ፡- ልጅ ሆኜ ብዙ ስፖርቶችን 
እየተጫወትኩ ነው ያደግኩት፡፡ ዳኝነቱ ግን 
ሰፈር ጨዋታ ሲኖር ታላላቆቻችን አጫውቱ 
ይሉን ነበርና በልምድ ገብተን እናጫውት ነበር፡
፡ ያው ፈርተን ነበር የምንዳኘው፡፡ የ90ዎቹ 
ፕሮጀክት ላይ ተመልምዬ የነበረ ቢሆንም 
ቤተሰብ እንድማር ብቻ ስለሚፈልግ ተከልክዬ 
ሰይሳካ ቀረ፡፡ በኋላ ላይ አሰልጣኙ አቶ ግርማ 
የዳኝነቱ ኮርስ ሲወጣ ኮርሱን እንድወስድ 
አደረጉ፡፡ የዳኝነት ሀሁ ያኔ ተጀመረ፡፡ ጊዜው 
1993 ላይ ነበር፡፡ ባህር ዳር ላይ 2ኛ ደረጃ 
ኮርስ ወሰድኩና የቀበሌ፣ የጤና ስፖርትና ባህር 
ዳር ውስጥ ያሉ ክለቦችን ማጫወት ጀመርኩ፡
፡ በወቅቱ በከተማችን የሃ/መላክ ተሰማ ዝና 
ይነገር ነበረና ሃ/መላክን ትሆናለህ ይሉኝ ነበር፡
፡ ሃ/የሱስ ሃ/መላክን ትሆናለህ ይሉኝ ነበር፡፡ ሃ/
የሱስ ሃ/መላክን ትሆናለህ በማለት ያበረታቱኝ 
ነበር፡፡ በወቅቱ ግን ሃ/መላክን በአይኔም አይቼው 
አላውቅም እንዲህ እያለ ጀመረ፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቀላል 
ነው በእርምጃ እየሄዳችሁ መምራት ትችላላችሁ ሁሉ 
ይባላል እውነት ነው?
ሃ/የሱስ፡- በጣም የሚገርመው ኢንተር 
ናሽናል ጨዋታና የኛ ሊግ ለንፅፅር የሚበቃም 
አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን 
በሙሉ 90 ደቂቃ ውስጥ በጣም ከሮጥኩ 8 
ኪሎ ሜትር ነው ኢንተርናሽናል ውድድር ላይ 
ወደ 12 ከ.ሜትር ቢያንስ መሮጥ ይጠበቃል፡
፡ የአገራችን ውድድር በጣም የቆመና መሮጥ 
የሚያስችል የኳስ ንክኪ ብቻ ያለበት በመሆኑ 
አላስቸገረኝም፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 
ለግጥሚያው ክበደት በላይ የሚያስቸግረው 
ባህሪው ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የጊዮርጊስና የቡና ጨዋታን መርተሃልና 
ፈትኖኛል ብለህ ታምናለሀ? 
ሃ/የሱስ፡- በተፈጥሮዬ ጫና ያለበት 
ጨዋታ ይመቸኛል፡፡ እኔ ከማጫወቴ በፊት 
የነበረው አካሄድ 3 ዳኛ ይመደቡና የተመረጠው 
የሚታወቀው ባለቀ ሽርፋራፊ ደቂቃ ላይ ነበር 
እኔ ስመደብ ግን ከቀናቶች በፊት ተነግሮኝ 
ስለነበር ተዘጋጅቼ መጣሁ፡፡ የህዝብ ብዛትና 
ጩኸት በአዕምሮዬ እንድበረታ ያደርገኛል፡
፡ እያጫወትኩ ጫና ሲሰማኝ እዘምራለሁ፡፡ 
ወይም የመጣልኝን ሙዚቃ ካለ አንጎራጉራለሁ፡
፡ የነርሱም ጨዋታ ተበላሽቶብኝም አያውቅም፡
፡ የሁለቱ ጨዋታ ክስ የሚበዛበት ቢሆንም 
እግዚአብሄር ይክበር አምላክ ሞገስ ሆኖኝ 
ተበላሽቶብኝ አያውቀም፡፡ 
ሀትሪክ፡- ለዳኞች የሚሰጠው ክብር በቂ ነው 
ማለት ይቻላል?
ሃ/የሱስ፡-ለሙያው ያለው ክብር ጥሩ ነው 
ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ 
ፕሪምየር ሊግን ሳጫውት አበሉ 100 ብር 
በነበረ ጊዜ ደርሻለሁ፡፡ አሁን ደግሞ 1000 
ብር ደርሷል፡፡ ያም ቢሆን ግን በቂ አይደለም 
ጊዮርጊስና ቡናን አጫውተን ከ350 ሺህ ብር 
በላይ ገቢ እየተገኘ የዳኛው አበል 1000 ብር 
ብቻ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ገና መሆኑን ያሳያል፡
፡ አሁን ከባህርዳር መጥቼ አ/አ ሳጫወት 
አበሉ 1000 ብር ነው፡፡ የትራንስፖርት ክፍያን 
ጨምሮ የሙያ መባሉ 1000 ይሆንና የሶስት 
ቀን ስለሚሰጥ 3000 ብር አገኛለሁ፡፡ አጠቃላይ 
እስከ 5ሺህ ብር ሊደርስ ይችላል፡፡ የሚገርመኝ 
ከሙያው ውጪ ይሄን እንደ አንድ የቢዝነስ 
ዘርፍ የሚያዩ ዳኞችን አይቻለሁ፡፡ ስራዬ ብሎ 
ይዞ ነገር ግን ለዲሲፕሊኑ ተገዥ ባይሆንና 
ገንዘቡን ብቻ ካሰበ የሙያ ክብሩ ሞቶ ሊገኝ 
ይችላል፡፡ አመራሮቹና ዳኞቹ ገንዘቡን ማግኘት 
እንጂ ሙያውን የማያስቀድሙ ናቸው ብዙ 
የሚወሩ ነገሮች አሉም፡፡ አዕምሮዬን ገንዘቡን 
ማስቀደም ከቻለ ችግር ይሆናል፡፡ ሙያ ቀመስ 
ያልሆኑ ችግሮች ዳኝነቱ ውሰጥ በብዛትም 
ይታያሉ፡፡
ሀትሪክ፡- በእግር ኳስ አሰልጣኝነት ፒ ኤች ጂ 
ያለው አርቢትር አለ?
ሃ/የሱስ፡- በአገራችን ደረጃ የለም፡፡ 
ማስተርስና ዲግሪ ያላቸው ዳኞች አሉ፡፡ ፒ ኤች 
ዲ ግን ያለው የለም፡፡
ሀትሪክ፡- የፊፋ ኢንተርናሽናል ዳኛ የሆንከው 
መቼ ነው?
ሃ/የሱስ፡- በ2004 ዓ.ም የኢንተርናሽናል 
ባጅ ተቀብያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ባለፉት አመታት የነበረህ የዳኝነት ጉዞ 
ምን ይመስላል ፈተናዎቹ አይብዙም ወይስ መንገዱ 
አልጋ በአልጋ ነበር?
ሃ/የሱስ፡- የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ 
በማንኛውም አጋጣሚ ዳኞች ውጭ አገር 
ወጥተው እንዲያጫውቱ ያደረገው ድጋፍ አለ 
ማለት ይከብዳል፡፡ በተለይ ከሌሎች አገራት 
ጋር ስናነፃፀረው የኛ የዳኘነት ኑሮ ከድጋፍ 
ይልቅ አሉባልታ የበዛበት ነው፡፡ የተለያየ 
አገራት ባለሙያዎች ኮርስ ሊሰጡ ሲመጡ 
አንዱ የኮሚቴ አባል ሌላውን እንዲህ አድርጎ 
እያሉ በማውራት የአገርን ስም ዝቅ ሲያደርጉ 
ከመታየቱ ውጩ ዳኞችን በተመለከተ ድጋፍ 
እንዲያገኙ ሲጠይቁ ወይም ሲያግባቡ 
አይታዩም፡፡ ይሄ በፌዴሬሽኑም ሆነ በኮሚቴው 
ደረጃ አልተሰራም፡፡ ኢንተርናሽናል ዳኞች እኔና 
በአምላክ ተሰማ ነበርን አሁን ግን 7 ደርሰናል፡
፡ ወደ 7 ማደጉ ለአገር ቢጠቅምም ጥራቱ ላይ 
መተኮር አለበት ባይ ነኝ፡፡ 7ቱ ዳኛች ከአገር 
ወጥተው በብዛት እንዲያጫውቱ መደረግ 
አለበት፡፡ በዚህ ደረጃ ጥሶ የወጣው በአምላክ 
ተሰማ ብቻ ነው፡፡ በርሱ ደረጃ የሚከተል 
አንድም ዳኛ አልተገኘም፡፡ ምክንያቱም 
መተጋገዙ በፍፁም የለም፡፡
ሀትሪክ፡- መረጃ ሳሰባስብ አንተና የኮሚቴው 
ሰብሳቢ አቶ ልዑል ሰገድ በገሻው መሃል አለመግባባት 
እንዳለ ሰማሁ እውነት ነው?
ሃ/የሱስ፡- እውነት ነው፤ ሁለታችን መሃል 
መልካም ግንኙነት የለም፡፡ ተመርጠው ከገቡበት 
2006 ጀምሮ ግንኙነታችን ጥሩ አይደለም፡
፡ ምክንያቱም ደግሞ ለቀድሞው አመራሮችና 
ለዳኞች ኮሚቴ ድጋፍ ይሰጣል በሚል ምክንያት 
ነው፡፡ አዲሱ አመራር ቦታውን እንደተረከበ አቶ 
ልዑል ሰገድ መንገድ ትራንስፖርት አዳራሽ 
በተካሄደው ስብስባ ወደ 200 የሚጠጉ ዳኞች 
ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ 10 የአዲስ አበባ ዳኞች 
የቀድሞ ኮሚቴ በደለን፣ ጥሩ አልሰራም የሚል 
ቅሬታ አቀረቡ፡፡ 11ኛ የመናገር እድል ሳገኝ በፊት 
የነበረችው ወ/ሮ ጥሩወርቅ ብርሃኑ ስትመጣ 
ሞቅ ባለ አቀባበል ነው ሁሉም የተቀበላት፡፡ 
ከወረደች በኋላ ደግሞ ይኸው ስድብና ቅሬታ 
ተሰማ፡፡ የቀድሞ ኮሜቴ ከአ/አ ዳኞች ጋር 
ያለው ቅሬታ በጥናት መታየት አለበት፡፡ አሁን 
ለናንተ ስለተጨበጨበ ልትገረሙ አይገባም 
የነገውን ማን ያውቃል ብዬ መናገሬ ለአቶ 
ልዑል ሰገድ አልተዋጠላቸውም፡፡ ሁሉንም 
መርምሩ ማለቴ ከዘር ድጋፍ ጋር አያያዙና 
የተወሰነ ጊዜ ምደባ ላይ ተዘለልኩ፡፡ ማጫወት 
አልቻልኩም ያው በተለመደው የዝምታ ቅጣት 
ታገድኩ፡፡ 2 ወር ሙሉ ሳልመደብ 3ኛ ወር ላይ 
ሄጄ ስናገር አቶ ልዑል ሰገድ አልተመደብክም 
እንዴ? ብሎ አፌዘብኝ፡፡ በኋላ ሃ/የሱስ የአዲስ 
አበባ ዳኞች አይችሉም ብሎ ተናገረ ተብሎ 
ትርጉም ተሰጠው የበፊቱ ኮሚቴን ሃ/የሱስ 
ደግፎ ይህንን ኮሚቴ አልቀበልም ብሏል የሚል 
ዘር ተኮር ደካማ አስተሳሰብ በመሆኑ ብዙም 
አልተገረምኩም፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ግንኙነታችን 
ጥሩ አይደለም፡፡
ሀትሪክ፡- የማይረሱ ገጠመኞችን እስቲ አውጋን?
ሃ/የሱስ፡- ከምደባቸው ክልከላ ውጪ 
በየአመቱ የሚመጣው በሬ ወለደ ያስበረግጋ 
ቸዋል፡፡ 2007 ላይ ምስጐን ተብዬ ብሸለምም 
መሰናክል የበዛበት አመት ነበር፡፡ ዳኝነት ለማቆም 
እስክወስን ድረስ የተገደድኩበት አመት ነበር፡፡ 
ጋዜጠኞችም ጠርቼ የመጨረሻዬ ጨዋታ ነውና 
ኑና እዩ አስተያየችሁን እፈልጋለሁ እስክልም 
ደርሼ ነበር፡፡ በሙያ ጓደኞቼ ጥረት ተመለስኩ 
እንጂ በኮሚቴው በተለይ ደግሞ በ3ቱ አበላት 
(አቶልዑል ሰገድ በጋሻው፣ አቶ መብራቱ አዲስና 
አቶ ይድነቃቸው (ቦቸራ) በጣም የተገፋሁበት 
አመት ነበር፡፡ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴም ሳይረሳ፡፡ 
ሸረፋ ደሌቾንና ክንዴ ሃይሉን በዚሁ አጋጣሚ 
ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ 2007 ያንግ ታለንት 
ኮርስ ተብሎ ስልጠና መጣ፡፡ የተመደበው ደግሞ 
በላይ ታደሰ ሲሆን ካፍ በስሙ የላከለበት ነበር፡
፡ እኔ ግን በ2004 ስገባ እድሜዬ 26 ስለነበር 
እድሉን በየአመቱ እጠብቅ ነበር፡፡ የውጪ ሰዎች 
ባዘዘው እያሉ ይጠራሉ በአካል ግን አያውቁኝም 
የሚስሉት በጣም ትልቅ ሰው አድርገው ነበር፡
፡ ሲመጡ ተዋወቅኳቸው ራሴንም አስተዋወኩ 
ያኔ ሃ/የሱስ በላይ ታደሰን አስቀርቶ ሊሄድ 
ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አቶ ይግዛው ብዙአየሁ 
አግዘውታል ተብሎ ጉዳዩ እነ አቶ ጁኒየዲን 
ባሻ ድረስ ደረሰ፡፡ ነገር ግን ውሸት ነበር፡፡ 
ዝም ብሎ የቀረበ አቤቱታ እንደሆነ ብናገርም 
ይጣራል ተብሎ አሁንም ምደባው ቆመ፡፡ 
ወሬ የት እንደሚጠራ ባይገባኝም ከማጫወት 
ታገድኩ፡፡ አቶ ይግዛውን አንድ አመት ሃ/የሱስን 
6 ወር ሊቀጡ ይገባል ተብሎ ሊወስኑ ሲሉ 
ውሸት መሆኑ ተረጋገጠና ቀረ፡፡ በላይ ታደሰም 
ስልጠናው ላይ ሄደና ወሬው በሬ ወለደ ሆነና 
ቀረ፡፡ በዚህ አመት የነሰለሞን ግሩፕ ተነሳና 
ሃ/የሱስን የማጥፋት ዘመቻ ተጀመረ፡፡ አ/አ 
ከተማ ከሱሉልታ ሳጫውት ለአ/አ ከተማ ሪጎሬ 
ሰጠው ርግጠኛ የሆነ ተገቢ ውሳኔ ነበር፡፡ ነገር 
ግን ኮሚሽነሮች ሪጎሬ ነው አይደለም በሚል 
ከህጉ አንፃር ሳይሆን የህዝቡ ጩኸት ካለ በኔ 
አስተየየት ለግምገማ መስጠት አልነበረበትም 
ይላሉ እና ሪጎሬው አከራካሪና ለግምገማ 
ተጠራሁ፡፡ ሂደቱን ቀርጨ ይዤው እንደነበር 
ሲይውቁ ስለሪጎሬው ሳይነሳ ቀረ፡፡ ያ ሳይሆን 
ሲቀር ጨዋታ ከመሃል ሲጀመር አስደግሜ 
ነበርና ለምን አስደገመ ብሎ ኢንስፔክተር 
ጌታቸው የማነብርሃን ሲናገር ደነገጥኩ አፈርኩ፡
፡ ነገር ግን በቀድሞው አረንጓዴው መፅሃፍ 
ገፁ 31 ላይ የተፃፈውን ህግ አነበብኩ አቶ 
ሰለሞንና ኢንስፔክተሩ ጌታቸዉ ህግ ይጠቅሳሉ 
ብለው አስበው ስላልነበረ ደነገጡና ታለፈ፡፡ 
መምህር ነኝ አነባለሁ ስለዚህ ክፍተት ሊያገኙ 
አይችሉም፡፡ ሌላው የሚገርመው የሲዳማ ቡና 
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ሞውሪኖ ነበር፡፡ 
ቀድሞ በነበራው የአዳማ ጨዋታ ላይ ተበደልን 
ብለው ቅሬታ አቅርበዋል፡፡ በወቅቱ እኔ የመሃል 
ዳኛ ኮሚሽነሩ ደግሞ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ነበሩ፡፡ 
ከፌደሬሽኑ ደግም አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ ተወክለው 
ተገኝተዋል፡፡ ከጨዋታው በፊት በነበረ ውይይት 
ላይ በአጋጣሚ ጉዳዩ ተነሳና እንደሞውሪንሆ 
ተጨዋቾቻችን ቀይ ካርድ ማየት አልነበረበትም፡
፡ ምራቁን ተፋ ካለ በቀጥታ ቀይ ካርድ እንጂ 
በሁለተኛ ቢጫ ካርድ መውጣት አልበረበትም 
ሲል ዝም ማለት አልቻልኩም፡፡ ዳኛው ልክ 
ነው ተጨዋች ተቃውሞ አሰምቶ ምራቁን ወደ 
መሬት ከተፋ በምልክት መቃወም ማለት ነው፡
፡ ይሄ በቢጫ ካርድ ነው የሚታለፈው ዳኛው 
ላይ ከተፋ ግን ቀይ ካርድ ያያል በዚህ አካሄድ 
ዳኛው ልክ ነው፡፡ ኮሚሽነሩ ሆነ ዳኛውን 
አላውቀውም ነገር ግን ውሳኔው ትክክለኛው 
ነው ስል ሞውሪንሆ ሆነ አቶ ዮሴፍ ተቀበሉት፡
፡ አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ ደግሞ ዳኛው በቀይ 
ካርድ ማባረር ነበረበት፣ ኮሚሽነሩ መፃፍ 
ነበረበት የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው እነ አቶ 
ዮሴፍንም አሳምነው ነበር፡፡ ከኔ ጋር ሲያወሩና 
ሃሳቡን ሲቀበሉ ግን አቶ ሰለሞን ተናደዱ፡፡ ለካ 
ኮሚሽነሩ አቶ ግዛቴ ነበሩና ለቅርብ ጓደኛው 
ግዛቴ ሲል ተከራከረ፣ ብሎ ወሬውን ነዛው 
የግዛቴን ክስ ለማስተባበል እንዲህ አለ ተብሎ 
ተወራ፡፡ በወቅቱ ከጨዋታው በኋላ አቶ ሰለሞን 
ሪፖርቱን ሆቴል ናና አሁኑኑ ስጠኝ ሲል አይ 
ደክሞኛል ከቻልክ ራስህና አለበለዚያ አ/አ ነው 
የምሰጥህ ብዬ መለስኩለት፡፡ 90 ደቂቃ ሙሉ 
ደክሞኝ እንደገና ርሱን በመፈለግ ተገቢ ነው 
ብዬ ባለማመን አላደረግኩትም፡፡ ይህንንም 
አላከበረኝም ብሎ ተረጎመው፡፡ ይሄ ጉዳይ 
እነቦቸራና መብራቱ ሲሰሙ ጥጋቡ አልበረደም 
ተባልኩና እንደገና ሳላጫውት ለረጅም ጊዜ 
ከምደባ ውጪ ሆንኩ፡፡ ሁሌ የሚገርመኝ 
የተረበሹ ጨዋታዎች ከተካሄዱ በኋላ ቀጣይ 
ጨዋታ ላይ የምሄደው እኔ መሆኔ ነው፡፡ 
ሲዳማ ቡና አዳማ ላይ ተበደልኩ ባለ ማግስት 
የተላኩት እኔ ነበርኩ፤ ደደቢት ከኢትዮጵያ 
ቡና ሲጫወቱ የዳኝነት ችግር ደረሰ ብሎ ቡና 
ቅሬታ ባቀረበ ማግስት ያጫወትኩት እኔ ነኝ፡
፡ የአርባምንጭና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ተፈርቶ 
ስለነበር የተመደብኩት እኔ ነኝ፡፡ ችግር በነበረበት 
ጨዋታ ቀጣይ የምመደበው እኔ ነኝ፡፡ በፀጥታ 
አካሄድ ታግጄም ቢሆን ረብሻ ካለ በቀጣይ 
የምመደበው እኔ በመሆኔ በደንብ መዘጋጀት 
ነበረብኝ፡፡ እኔን ጨዋታ ላይ ለመመደብ ረብሻ 
ያስፈልግ ነበር (ሳቅ በሳቅ) ደስ የሚለኝ ግን 
እመብርሃንን ጠይቄ ስለምገባ አምላክ ደግሞ 
በሞገስ ያግዘኛልና ጨዋታው አይበላሽብኝም 
ነበር፡፡ 
ሀትሪክ፡- ታመምክ ተብሎ ከምደባ ውጭ 
የሆንክበት ጊዜ አለ…… በዚያ ላይ ለፀሎት ሄደህ 
ዳኛ አሰለጠንክ ተብለህ ልትቀጣ የነበረበትስ አመት 
ትዝ ይልሃል?
ሃ/የሱስ፡- በየአመቱ ውድድር ሊጀመር 
ሲልና እረፍት ሲደረግ ቤ/ክ መሄድ እወዳለሁ፡፡ 
በወቅቱ ወደ ዘብር ገብርኤል ለፀሎት ሄጃለሁ፡
፡ እዚህ ግን የተወራው ባህርዳር የሄደው 
ያለፌዴሬሽኑና ኮሜቴው እውቅና ለዳኞች 
ስልጠና እየሰጠ ነው ብለው ሊቀጡ ለካ 
አሰፍስፈዋል፡፡ አ/አ ስመጣ ነገሩ ጦዞ ጠበቀኝ፡
፡ ችግር ሲፈጠር አቶ ልዑልሰገድ ማናገር 
የማይቻል ነው፡፡ መግባባትም አይችልም፡
፡ አቶ ሸረፋ ደሌቾ ጋር ደውዬ ስነግረው 
ስልጠና ብትሰጥ ችግሩ ምንድነው አለኝ ይሄኮ 
ለኮሚቴው እገዛ እየሰጠህ ነው ማለት ነው 
አለኝ…. አሁንም በዚህ ምክንያት ከምደባ 
ውጪ ሆንኩ፡፡ ተበሳጨሁና ማስረጃ በሌላው 
ወሬ እንዴት ከምደባ እዘለላለሁ፡፡ ሰዎች የወሬ 
ሰለባ ሲያደርጉኝ ኮሜቴው እንዴት ድጋፍ 
አያደርግልኝም ብዬ ተናገርኩ፡፡ ተደጋጋሚ ወሬ 
ያውም ያለ መረጃ እየተወራ አቶ ልዑል ሰገድ 
ነገሩ ምንድነው ብለው ካልተነሱ ችግሩ ያው 
እርሳቸው ጋር ነው ማለት ነው፡፡ ሌላ ጊዜ 
ከትሬኒንግ በኋላ የስፖርት ማሳጅ ይመከራል፡
፡ አንዴ ማሳጅ ልውስድ ስሄድ አቶ ሃ/የሱስ 
በጣም ተጎድቷል፡፡ ጉዳቱ ከፍ ያለ በመሆኑ 
ምደባ እንዳይመደብ ተብሎ ተነገራቸው… 
ሄጄ ስጠይቀው ታመሃል ተብሎኮ ነው ሲለኝ 
ተቆጣውና እኔ ነኝ ታምሜያለው ማለት 
ያለብኝ ወይሥ አለበለዚያ ተደውሎ መጠየቅም 
ካለብኝ እኔ ነኝ፡፡ 6ኛ ክፍል ካመመኝ ውጪ 
አሞኝ አያውቅም እግዚአብሄር ይመስገን ጉዳት 
ሲያጋጥመኝ ወይም የማይመች ሁኔታ ሲከሰት 
ከአምላክ ጋር ሆኜ ራሴን የማክምበት መንገድ 
ስላለ ከህመም ራቅ ብያለሁ ብዬ መለስኩ፡፡ 
በአቶ ልዑልሰገድ የምደባ ሂደት አንተ ተነስተህ 
ትምህርት አለኝ ብሏል ብለህ ብትነግረው 
ከምደባው ያነሳኛል (ሳቅ በሳቅ) ከእኔ ማረጋገጫ 
አይታሰብም፡፡ ይሄ ደግሞ ልቤን አድምቶታል፡
፡ በዚህ ሁሉ ተበሳጭቼ ከዳኝነቱ አለም 
ያልተገለልኩት ጓደኞችን ለማግኘትና ከነርሱ 
ጋር ለመስራት ስል ብቻ ነበር፡፡ 
ሀትሪክ፡- ኩራተኛ ነህ… ይሉሃል… በተለይ 
ከኮሚሽነሮች ጋር አትግባባም ትባለለህ… ለምን…?
ሃ/የሱስ፡- ከኮሚሽነሮች ጋር ፀብ የለኝም፡
፡ ነገር ግን መናገር ያለብኝ (ስም ጠቅሷል) 
ኮሚሽነር ሆነው ከተመደቡ እነርሱን መጋበዝ 
ግዴታ ይሆናል፡፡ ሁሉም ዳኞች በግድ 
ያደረጉታል፡፡ በተለይ ከኢንተርናሽናል 
ጨዋታ መልስ የግድ መጋበዝ እንዳለብህ 
ነው የሚታሰበው…እነሱም ኮሚሽነር ከሆኑ 
መጋበዝና አልጋ መክፈል የግድ ነው፡፡ ሁለቱ 
ለኔ ከ7 ጊዜ በላይ ከሚሽነር ሆነውኛል፡፡ ያንን 
ነገር ከኔ ጋር አላገኙትም፡፡ በፍፁም አልጋብዝም፡
፡ ቋንቋችን ስፖርት ቢሆንም ተመሳሳይ ነገር 
ስለማናወራ ብዙ ሰአት ከነርሱ ጋር አላሳልፍም፡
፡ ጨዋታው ካለቀ በኋላ ወደ በቴ ነው 
የምሄደው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሃ/የሱስ የታንክ ፍሬን 
ነው ይላሉ፡፡ ከሆነም አዎ ለመጋበዝ አለመፈለግ 
ስላበሳጫቸው በኔ ተቃራኒ መሆን ይወዳሉ፡፡
ሀትሪክ፡- ስራ አስፈፃሚ ለመሆን ታስባለህ 
እንዴ… እንዲህ ሲባል ሰማሁ?
ሃ/የሱስ፡- (ሳቅ) ከየት ሰማህ? ተዘጋጀተህ 
ነዋ የመጣኸው? ፒ ኤች ጂ የሚማረው ስራ 
አስፈፃሚ ለመሆን ሲል ነው ተባለ፡፡ እኔ እኮ ዳኛ 
ነኝ፡፡ የዳኞች ኮሚቴ ፀሃፊ የሆነው አቶ በቀለ 
ደወለና የአማራ ክልል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 
አባል ነህ አሉ ይሄ ደግሞ ልክ አይደለም ሲለኝ 
ተማሪ ነኝ የማነብበት ሰአትንኮ የለኝም ውሸት 
ነው አልኩት፡፡ በዚህ ወሬ የተነሳ ይጣራ ተብሎ 
የጨዋታ እገዳ ውስጥ ገባሁ..(ሳቅ) እስኪጣራ 
ተብዬ ስታገድ ለሸረፋ ስደውል ያጣራና ለምን 
ብሎ እንዲስተካከል ይደርጋል፡፡ ይሄና ሌሎች 
ወሬዎች ከሰብሳቢው ጋር ያለኝን ግንኙነት ሻካራ 
አደረገው፡፡ ያው መጣብን መጡብኝ ማለቱ ነው 
በተረፈ ግን አስቤው አላውቅም፡፡ 
ሀትሪክ፡- የአመቱ ኮከብ ተብለህ የተመረጥከው 
ታድያ በአጋጣሚ ነው ማለት ይቻላል?
ሃ/የሱስ፡-(ሳቅ በሳቅ) በ2007 ኮከብ ዳኛ 
ተብዬ በነበረበት ወቅት በባሀርዳር ከተማ 
ከአማራ ውሃ ስራጋር የተደረገውን ጨዋታ 
የመራሁት እኔ ነኝ፡፡ ጨዋታው ጠንካራና 
የደርቢ ግጥሚያ ሲሆን በጨዋታው መሃል 
ባህርዳሮች ከኔ ልዩ ጥቅም ፈልገው ነበር፡፡ 
85ኛው ደቂቃ ድረስ 1ለ0 እየመሩም ነበር፡፡ 
85ኛው ደቂቃ 16 ከ50 ውስጥ ጥፋት ተፈፀመና 
ሪጎሬ ለአማራ ውሃ ሰጠሁ፡፡ ለባህር ዳር ህዝብ 
ሲል ምናለ ቢተወው የሚል ወገን ተነሳ፡፡ ጥፋቱ 
እያየሁ በስመ የባህር ዳር ነዋሪነት ማታለል 
ባለመፈለጌ በሰጠሁት ሪጎሬ ጎል ተቆጠረና 1ለ1 
ተለያዩ፡፡ ማሸነፍ ቢችል ለባህር ዳር የተሻለ 
ጥቅም ስለነበር ብዙዎች ተበሳጩና የባህር 
ዳር አመራሮችም ለፌደሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ 
አስገቡ፡፡ ከጊዜ በኋላ እነ ልዑልሰገድ የአማራ 
ክልል ክለቦችን ሊያናግሩ ባህር ዳር መጥተዋል፡
፡ ደጋፊው ሃ/የሱስ ለማህተሙ ነው በሚልና 
ለህዝቡ ሲልስ ምናለ ቢተወው በሚል ሃሳብ 
ለሁለት ተከፍሏል፡፡ ጥፋቱ ነው አይደለም 
በሚለው ሳይሆን ምናለ ቢተወው እየተባባሉ 
ቆይተዋል፡፡ እነ ልዑልሰገድን ሲያገኙና 
ሲያናግሯቸው ቀድማችሁ ነግራችኋቸው ቢሆን 
ኖሮ ኮከብ ዳኛ ብለን አንመርጠውም ነበር 
ሲል የክልሉ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮችና 
ባለሙያዎች ሃ/የሱስ ኮከብ የተባለው 
እውነተኛና ታማኝ ስራ ስለሰራ እንጂ እናንተ 
ስለፈለጋችሁት ስላልፈለጋችሁት አይደለም 
በማለት መሳሳታቸውን ነገሯቸው፡፡ ኮከብነት 
በመልካም ፍቃድ እንጂ በሙያ ብቃት አይደለም 
ማለት ነው የሚል ተቃውሞ ቀረበባቸው ይሄን 
አልረሳውም፡፡ 
ሀትሪክ፡- ተደጋጋሚ ጨዋታ ትመደብና እንደገና 
ትቀየራለህ ምንድነው ምክንያቱ?
ሃ/የሱስ፡- በምደባ 3 ጊዜ ተቀይሬይለሁ፡
፡ የመጀመሪያው ምደባ ወላይታ ዲቻ ከጅማ 
አባቡና ጋር ነበር፡፡ እንደሁልጊዜው በስልክ 
ነገረኝ፡፡ ወደ ጅማ ለመሄድ ትኬት ቆረጥኩ፡
፡ እንደገና ተደወለና ያንተ ምደባ ተሰርዟል 
ተባልኩ፡፡ እሺ ብዬ 300 ብር ተቀጥቼ ትኬት 
መለስኩ፡፡ እንደገና ደወሉና ትኬትህን አስተካክል 
እንደገና ተመድበሃል ብለው ሲደውሉ ትኬት 
ቆረጥኩ፡፡ እንደገና ደወሉና አሁንም ይቅርታ 
ተቀይረሃል አሉኝ፡፡ ተቀየርኩ ኮሚቴው 
ያውቃል እንዴ ብዬ ለሸረፋ ደወልኩለት፡፡ 
አይ አላውቅም መመደብህን እንጂ መቀየርህን 
አላውቅም አለኝ፡፡ ለካ አቶ ልዑል ሰገድ ከአቶ 
አበበ ገላጋይ ጋር ተነጋገርው ነው የቀየሩት፡
፡ የሰሩት ስሌት ሊኖር ይችላል፡፡ እኔ ጋር 
ግን ሙያዬን ሰርቼ ነው መመለስ የምፈልገው፡፡
ሀትሪክ፡- ምክንያቱ ግን ምን ይመስልሃል 
የምትገምተው ነገር አለ?
ሃ/የሱስ፡- ከተመደብኩበት ጨዋታ የምቀ 
የረው ለምንድነው ብየ ለኮሚቴው ስጠይቅ 
የተሰጠኝ መለስ አንተ ለውንብድና አትመችም 
የሚል ነው ፡፡ በብቃት ማነስ አይደለም 
በአምላክም ሁለት ጨዋታ ተሰርዞበታል 
አሉኝ፡፡ ለጨዋታ የማትመቹ ዳኞች አላችሁ 
ካልተመቻችሁ ደግሞ ትሰረዛለችሁ አሉን፡፡ 
ከዚያ በኂላ ምደባ ሲሰረዝ ለምን ብዬ መጠየቄን 
አቆምኩ፡፡ ምክንያቱም አልመችማ ለኔ ትልቅ 
ክብር ነው፡፡ ድሬደዋ ከሐዋሳ ባደረጉት ጨዋታ 
እኔ ነበርኩ ትኬት ቆርጩ አ/አ ከመጣሁ 
በኂላ ተሰርዘሃል አሉኝ ዳኛ ኮሚቴ ይገናኛና 
ይመድባል ሌሎች ደግሞ ይሰርዛሉ ንግድ ባንክ 
ከኤሌክትሪክ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ተመደብኩ 
ደወሉና መሰረዜን ነገሩኝ የማላስፈልግባቸው 
ወቅቶች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁሉ አልፌ መስመር 
ሲያልፍ ነው ካንተ ጋራ ያወራሁት፡፡ 
ሀትሪክ፡- ኢንተርናሽናል ባጅ ተነጥቀሃል 
ምክንያቱ ደግሞ ወድቀሃል ተብሎ ነው በርግጥ 
መውደቅህ ተገቢ ነበር?
ሃ/የሱስ፡- ሲጀመር አልወደቅኩም ወድቀ 
ሃል ካሉኝ ደግሞ እንደሌሎች ዳኞች የድጋሚ 
እድል ሊሰጡኝ ይገባል፡፡ ወድቄያለሁ ብዬም 
ለአዕምሮዬ አልነገርኩትም፡፡ የድጋሚ እድል 
እንዲሰጠኝ ለማድረግ አቶ ልዑልሰገድን 
ለማናገር ብቻ ከባህር ዳር አ/አ መጣሁ ነገር 
ግን ሊያናግሩኝ አልፈጉም፡፡ እንደ ህፃን ልጅ 
አንዴ እዚያ አንዴ እዚህ ጠብቀኝ በማለት ፊት 
ለፊት ለማናገር ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው 
ለፌደሬሽኑ ማመልከቻ ባስገባ የተሰጠኝ ምላሽ 
የለም ወድቀሃል ብለው ከነገሩኝ የድጋሚ 
ሊሰጡኝ ይገባል ውጪም ሄጄ ወይም ካርሎስ 
ሲመጣ ሙሉ ወጪ 50 ሺህ አካባቢ ከፍዬ 
ልፈተን ስል እንቢ አሉ፤ ከላይ ያለው ቁርሾ አቶ 
ልዑልሰገድ ውስጥ ስላለ በእንቢተኝነት ፀንቶ 
ከልክሎኛል፡፡ እንደ አገር እንደሙያ ድጋፍ 
ሊያደርጉልኝ አልፈቀዱም፡፡ 
ሀትሪክ፡- ከፕሬዝዳንቱ አቶ ጁነዲን ባሻስ 
ያገኘኸው ምላሽ ምንድነው?
ሃ/የሱስ፡- ፕሬዝዳንቱ አቶ ጁነዲን ባሻ 
ያናገርኳቸው ቢሆንም ልክ እንደ አንድ 
አመራር በስራቸው ያለው አካል አካሄዱን ሲስት 
አይሆንም ማለት ግን አልቻሉም፡፡ ድጋሚ 
የመፈተኔን ነገርና ለወጪው ችግር የለም 
የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ አቶ ልዑልሰገድን 
ስጠይቀው አንተን ለማናገር ዝግጁ አይደለሁም 
ከፈለግክ ኮሜቴውን ይደውልልሃል አለኝ፡፡ 
ከዚያ ውጪ ለዋና ፀሃፊው አቶ በቀለ ደውሎ 
ሃ/የሱስ ወደ ስቴድየም እንዳይመጣ፣ ማንንም 
ኮሚቴ እንዳያገኝ፣ የስራ አስፈፃማው ኮሚቴ 
ጋር ሄዶ የድጋፍ እድል ይሰጠኝ እንዳይል 
ተብለሃል ብሎ የልዑል ሰገድን ቃል ነገረኝ፡፡ 
እዚህ ድረስ መድረሱ ግርም ብሎኛል ስቴድየም 
አትድረስ ማለቱ አይገርምም? ኮማንድ ፖስቱ 
ተነስቷል፡፡ ገደቡም የለም ህገ መንግስቱንም 
የዘነጉት ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የብዙ ሰው 
ርዕስና መነገገሪያ መሆን ባለመፈለጋቸው ሰው 
እንዳላገኝ አዘዋል፡፡ 
ሀትሪክ፡- እንግሊዘኛ ቋንቋ የማይናገሩ ዳኞችን 
ይንቃል.. ሃ/መላክና ቸርነትን ቋንቋውን አይችሉም 
ብሎ ተችቷል የሚል ቅሬታ ሰማሁ እውነት ነው?
ሃ/የሱስ፡- ማንንም ዳኛ ንቄ አላውቅም፡
፡ ነገር ቃል ኮንግራ ያለኝ ፈተኙ የገባሁበትን 
ሰአት ደምሮ 3925 ሜትር ነው የሮጠው ብሎ 
መውደቄን ሲነግራቸው ቸርነትና ሃይለ መላክ 
ለምን ብለው ሊጠይቁ አልፈለጉም፡፡ ምክንያቱም 
መናገርም አይችሉም ተናግረውም ማሳመን 
አቅቷቸዋል ማለት ነው፡፡ ሃ/መላክ ያየውን 
ነገር መናገር አልቻለም በትክክልም የቋንቋ 
ችግር አለበት፡፡ ይሄ እውነት ነው ሁለቱም 
መናገር ማሳመን ቢችሉ ኖሮ አልወድቅም ይሄ 
ሁሉ ውጣ ውረድም አይኖርም ነበር፡፡ የሱዳን 
አርሶ አደር ኢትዮጵያ መጥቶ ማንንም ማዘዝ 
ይችላል፡፡ ምክንያቱም እንግሊዘኛ ቋንቋ ይችላላ 
ብዬ ተናግሬያለሁ፡፡ በቋንቋ ችሎታ ሊቅ ብለው 
ሰውዬውን ማክበር በእኛ አገር አመለካከት 
የሚታይ ነው እንግሊዘኛ ስለተናገረና ከነሱ 
የተሻለ ስለመሰላቸው ተቀበሉት እኔን ግን 
ሊያምነኝ አልፈቀደም ይሄን በግልፅ ብያለሁ፡
፡ ከዚያ ውጩ ቋንቋውን መናገር ለመግባባት 
ከመጥቀሙ ውጪ ሌላ ምንም አይጨምርም፡፡ 
ስለዚህ ሰውን ለማክበርና ሆን ለመናቅ እንግሊዘኛ 
ቋንቋ ወሳኝ አይደለም ባይ ነኝ፡፡ ለምንድነው 
የምንቃቸው? የሰውን ፐርሰናሊቲ በቋንቋ 
አልገምትም፡፡ በርግጥ የማይካደው ነገር መማሬ 
ጠቅሞኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት የእኔ ጓደኞች የሆኑ 
አብዛኛዎቹ አርቢትሮች 12ኛ ክፍልን የጨረሱ 
ናቸው፡፡ ወይም 10ኛ ክፍል ላይ የቆሙ ናቸው፡
፡ በጣም ትልቅ ተማሩ ከተባለ ዲግሪ ያላቸው 
ናቸው፡፡ የኔ ደግሞ እግዚአብሄር ይክበር ፒ 
ኤች ዲ ተማሪ ነኝ፡፡ ይሄ ደግሞ ለሰዎቹ ራስ 
ምታት ፈጥሯል፤ ይንቀናል የሚለው የራሳቸው 
አዕምሮ የፈጠረው ወሬ ነው እንጂ ማንንም 
አልናቅኩም፡፡
ሀትሪክ፡- ጨረስኩ… የመጨረሻ ቃል…?
ሃ/የሱስ፡- ዳኝነት እጅግ የተከበረ ሙያ 
ነው፡፡ ፖለቲካን የሚያነቃንቅ ህዝብን ሰላም 
የሚያደርግ ብዙ ሚሊየን ገንዘብ ኢንቨስት 
የሚደረግበት ሙያ ነውና ሊከበር ይገባል፡
፡ ከሰራን ገንዘብ ይከተለናል የሚል ፍልስፍና 
አለኝ፡፡ ገንዘቡን ካስቀደምን ግን ስራው ይበላሻል 
ዳኝነትን ማስቀደም ለህሊና ሰላም መስራት 
ይገባል እላለሁ፡፡ በእንባ ነው የምለምነው…
ዳኝነትን የሚመሩ ሰዎችና ባለሞያዎች ዳኝነትን 
ብቻ ያማከለ ወይም ሙያ ተኮር ስራ ብንሰራ 
መልካም ነው እላለሁ፡፡ ይሄ ነው ለአገር 
የሚጠቅም ስለሁሉም አመሰግናለሁ፡፡ በዚህ 
አጋጣሚ ሸረፋ ደሌቾና ክንዴ ሃይሉን፣በነበሩኝ 
የ4 አመታት ቆይታ አብረውኝ ለነበሩ ዳኝነቱን 
እንዳላቆም አብረውኝ ለነበሩ እንደ ትግል 
ግዛው፣ተመስገንና አበራ የመሰሉ ጓደኞቼ ሌሎች 
የሙያ አጋሮቼን ከልብ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ከአዘጋጁ፡- አርቢትር ኃይለየሱስ ባዘዘው 
የሰጡትን ቃለ ምልልስ ተከትሎ ዘገባውን 
ሚዛናዊ ለማድረግ በማሰብ የፌዴሬሽኑ 
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የአርቢትር 
ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ልዑልሰገድ 
በጋሻውን በጉዳዩ ላይ የሚሉት ካለ በሚል 
ባቀረብንላቸው ጥያቄ “ምንም አይነት ምላሽ 
መስጠት አልፈልግም” የሚል አጭር መልስ 
ሰጥተውናል፡፡ በቀጣይም እሳቸውም ሆኑ ሌላ 
ይመለከተኛል በሚል ማንኛውንም አካል በጉዳዩ 
ላይ ምላሽ መስጠት ከፈለገ የዝግጅት ክፍላችን 
በር ክፍት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...