መነሻ ገጽ ዜናዎች በስድስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ1-0 ድሎችን በማሳካት ሳምንቱን በድል አጠናቀዋል።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

በስድስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ1-0 ድሎችን በማሳካት ሳምንቱን በድል አጠናቀዋል።

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮ ኤሌትሪክ፣ ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድል ጣዕም ቀምሰዋል።

ኢትዮ ኤሌትሪክ 1-0 ሀላባ ከተማ

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ኢትዮ ኤሌትሪክ የጨዋታ ብልጫ ወስዶ ወደ ግብ በመድረስ የተሻለ እንቅስቃሴ አሳይቷል። ሆኖም ሀላባ ከተማ ግብ ሳይቆጠርባቸው የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽም የኢትዮ ኤሌትሪክ ጫና ቀጥሎ በ55ኛው ደቂቃ ካሌብ ስቲፍ በአስደናቂ ምት የጨዋታውን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል። ሀላባ ከተማ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም የኢትዮ ኤሌትሪክን መከላከል ሰብሮ ጎል ማስቆጠር አልቻለም።

ነገሌ አርሲ 1-0 ጋሞ ጨንቻ

ነገሌ አርሲ በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታ ብልጫ ወስዶ በ24ኛው ደቂቃ የጋሞ ጨንቻ ተከላካዮች ስህተት ተጠቅሞ መሐመድኑር ናስር ጎል አስቆጥሯል። ጋሞ ጨንቻ በአጋማሹ ወደ ግብ የሚያሰጋ ሙከራ ሳያደርግ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ብዙም ለውጥ ባልታየበት ጨዋታ ነገሌ አርሲ ወደ ግብ በመድረስ የተሻለ ነበር። ጋሞ ጨንቻ የአጥቂ እንቅስቃሴውን ማሻሻል እና ወደ ጨዋታው መመለስ ባለመቻሉ በአንድ ጎል ልዩነት ተሸንፏል።

ፋሲል ከነማ 0-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች እዮብ ተስፋዬ ያመቻቸውን ኳስ አናንያ ጌታቸው ወደ ጎልነት ቀይሮ ቡድኑን መሪ አድርጓል። በፉክክር የተሞላ የመጀመሪያ አጋማሽ በንግድ ባንክ መሪነት ተጠናቋል።
ፋሲል ከነማ በሁለተኛው አጋማሽ የማጥቃት ጥረቶቹን ቢያጠናክርም የንግድ ባንክን ጥብቅ መከላከል ሰብሮ ጎል ማስቆጠር አልቻለም። በመጨረሻ ደቂቃዎች ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን ጠብቆ ሙሉ ሶስት ነጥቡን ይዞ ወጥቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናአዳማ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና በመጨረሻ ደቂቃ ጎል አዳማ ከተማን አሸነፈ

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን 2-1 በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥቦችን ወስዷል።...

ባህርዳር ከተማኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ባህር ዳር ከተማ በሶስት ጎል ሶስት ነጥብ አሳካ!

በአቤኔዘር አበበ ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3-1 በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ...

ሀዋሳ ከተማሸገር ከተማኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሸገር ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና በተመሳሳይ ጎል አሸነፉ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም. የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን...