በአቤኔዘር አበበ
ባህር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ መድንን 3-1 በማሸነፍ ሙሉ ሶስት ነጥብ ወስዷል።
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ባህር ዳር ከተማ ኳስን በመቆጣጠርና በተሻለ የጨዋታ አቀራረብ በተቃዋሚው ላይ ብልጫ ወስዷል። በ10ኛው ደቂቃ ዩዳሄ ዳዊት ከቅጣት ምት የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር የቡድኑን የጎል ሂሳብ ከፍቷል።የኢትዮጵያ መድን በረኛ ኪትካ ጅማ ላይ በሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት አንተነህ ተፈራ ወደ ጎልነት በመቀየር ባህር ዳር ከተማ 2-0 እየመራ ዕረፍት ወጥተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮጵያ መድን የተሻለ አጀማመር በማድረግ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ተንቀሳቅሷል። በ69ኛው ደቂቃ በባህር ዳር ከተማ በረኛ በአሸናፊ ሐፋቱ ላይ በተሰራው ጥፋት የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ወገኔ ገዛኸኝ በመምታት የመድንን የመጀመሪያ ጎል አስቆጥሮ የጨዋታውን ውጥረት ጨምሯል።ሆኖም ባህር ዳር ከተማ የድል ሶስት ነጥቡን ከእጁ ሳያስወጣ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተቃረበበት 90+4ኛው ደቂቃ ደሳለኝ አሻግሬ የማሳረጊያ ጎል በማስቆጠር የቡድኑን ድል 3-1 አረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ