የማላዊ ዜግነት ያላቸው ዳኞች የወልዋሎ እና አልሀሊ ትሪፖሊን የካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ጨዋታን ይዳኛሉ።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ነገ ከሊቪያው አልሀሊ ትሪፖሊ ምሽት 2 ሰዓት ላይ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ መርሀግብሩን ያከናውናል። ወልዋሎ በሜዳው ማድረግ የነበረበትን ጨዋታ የፋይናንስ ድጋፍ በማግኘቱ ከሜዳው ውጪ ለማድረግ የተገደደውን ይህንን ጨዋታ የማላዊ ዜግነት ያላቸው አራት ዳኞች ይመሩታል።
በመሐል ዳኝነት ዴቪድ ቺኖኮ በረዳት ዳኝነት ደግሞ ላሜች ሙቡሉማ እና ቴምፖ ፖንዳማሊ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ኢስተር ብራይት ካሊኮሀ በጣምራ ይመሩታል።
አስተያየት ይስጡ