መነሻ ገጽ አዳማ ከተማ ሪፖርት | አዳማ ከተማ የሊጉን መክፈቻ በድል ጀመረ
አዳማ ከተማኢትዮ-ኤሌክትሪክዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

ሪፖርት | አዳማ ከተማ የሊጉን መክፈቻ በድል ጀመረ

አጋራ
አጋራ

በአቤኔዘር አበበ

አዳማ ከተማ ከ2013 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ አሸናፊ ሆኗል።

በፕሪምየር ሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቢኒያም አይተን ባስቆጠራት የፍፁም ቅጣት ምት ጎል አዳማ ከተማ 1ለ0 አሸናፊ ሆኗል።


ጨዋታው በሁለቱም ቡድኖች የተለያዩ የግብ ሙከራዎች የታዩበት ሲሆን አዳማ ከተማዎች በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት በመቀየር መሪ መሆን ችለዋል። 29ኛው ደቂቃ አዲሱ የኤሌክትሪክ ፈራሚ አካሉ አትሞ አቡበከር ሳኒ ላይ በሳጥን ውስጥ በሰራው ጥፋት የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወጣቱ አጥቂ ቢኒያም አይተን አዳማ ከተማን በዳሚ አድርጓል።


ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ግብ ካስተናገዱ በኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት አድርገዋል። 31ኛው ደቂቃ አብዱልመጂድ ሁሴን ያደረገውን ሙከራ ግብ ጠባቂው አላዛር ማርቆስ አምክኗታል። በቀጣዮቹ ደቂቃዎችም ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ሲጥሩ አዳማዎች የተገኘውን መሪነት ለማስጠበቅ ተግተው ታይተዋል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው በቀጠለበት ቀጥሎ አዳማ ከተማ አህመድ ሁሴን የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ግብ ጠባቂ አሊዮንዜ ናፍያን ከግብ ክልሉ ወጥቶ ያደረገበት ሙከራ በኤሌክትሪክ በኩል የአዳማ ከተማን መከላከያ ሰብሮ ወደ ግብነት የሚቀየር ዕድልን ማግኘት አልቻለም። በተቃራኒው አዳማ ከተማ የጨዋታውን መሪነት ሳያጣ የቀረበለትን ውጤት እስከ መጨረሻው ደቂቃ ማስጠበቅ በማስጠበቅ በአዳማ 1ለ0 አሸናፊነት ተቋጭቷል። አዳማ ከተማ ከ6 አመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ነው በሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ አሸናፊ የሆነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...