መነሻ ገጽ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የክለቦች ዝግጅት | አዳማ ከተማ
ቅድመ ውድድር ዝግጅትአዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የክለቦች ዝግጅት | አዳማ ከተማ

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው አዳማ ከተማ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በ2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ደካማ የውድድር ዘመን በማሳለፍ በመጨረሻው የጨዋታ ሳምንት በሊጉ መሰንበታቸውን ካረጋገጡ ክለቦች መካከል አንዱ አዳማ ከተማ እንደነበር ማስታወስ ይቻላል። ክለቡ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ መሪነት አመቱን ቢጀምርም 33 ነጥቦችን በአሰልኙ ስር ካሳካ በኋላ በድንገት ከሀላፊነት መነሳታቸውን ተከትሎ ረዳት የነበረው ዳዊት ታደለን በዋና አሰልጣኝነት ሚና በመቅጠር የተሻለ ቁመናን ይይዛል ተብሎ ቢታሰብም ክለቡ ግን 13 ነጥቦችን ብቻ በአሰልጣኙ ስር አሳክቶ ከመውረድ መትረፉን ያረጋገጠው በመጨረሻው የሊጉ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን 3ለ2 በመርታት ነበር።

ካደረጋቸው 38 ጨዋታዎች 10 አሸንፎ 16 የአቻ ውጤት አስመዝግቦ 12 ሽንፈት በማስተናገድ 35 ጎል በተጋጣሚው ላይ አሳርፎ 39 ጎሎችን ደግሞ በማስተናገድ በ4 የጎል ዕዳ 46 ነጥቦችን በመያዝ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የ2018 የውድድር ዘመኑን ማጠናቀቅ የቻለው አዳማ ከተማ ካለፈው አመት ስህተቱ ራሱን አሻሽሎ ለመገኘት ለሲቢኢ የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ራሱን ማዘጋጀቱን ሀትሪክ ስፖርት ከክለቡ ያገኘችሁ መረጃ ያመላክታል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በክረምቱ አስቀድሞ ከአራት አመታት በፊት አዳማ ከተማን ማሰልጠን የቻለችውን ፋሲል ተካልኝን በድጋሚ በዋና አሰልጣኝነት በመሾም የአሰልጣኝ ቡድኑንም ጭምር በቀድሞው አንጋፋ ተጫዋች ደጉ ደበበ ረዳት አሰልጣኝነት እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ መሳፍንት ከሀድያ ሆሳዕና ሁለቱንም በአሰልጣኙ ፍላጎት በማካተት ቡድኑ ባለበት ጥቂት ክፍት ቦታ ላይም ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን በዝውውሩ ማካተትም ችሏል።

አዳዲሶቹን ስንመለከት ይሁን እንዳሻውን ከአርባምንጭ ከተማ ፣ አጥቂው ቦና ዓሊን በድጋሚ ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ የመስመር ተከላካዩ አሰጋኸኝ ጴጥሮስን ከመቐለ 70 እንደርታ ፣ አማካዩ ፍፁም አለሙን ከባህርዳር ከተማ ፣ የመስመር አጥቂው ዮሴፍ ታረቀኝን ደግሞ በድጋሚ ከሸገር ከተማ እንዲሁም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ የመሐል ተከላካይ ዩጋንዳዊው ዋሳዋ ጂኦፎሪ እና ሴኔጋላዊውን ግብ ጠባቂ አብዱላሂ ዲያኬቴን ከሀገሩ ክለብ ጃራፍ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ሲሆኑ መድሀኔ ብርሀኔ ጨምሮ ሁለት የውጪ ዜጋ ተጨማሪ ሁለት ተጫዋቾች ደግሞ ከክለቡ በድምሩ የለቀቁ አምስት ተጫዋቾች ሆነዋል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ መሪነት በክለቡ መቀመጫ ከተማ አዳማ ላይ ከነሀሴ 18/2018 ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሲሰሩ የከረሙት አዳማ ከተማዎ በጂም እና በሜዳ በቀን ሁለቴ ያለፉትን ሳምንታት ደግሞ በቀን አንድ ጊዜ ዝግጅታቸውን እየሰሩ ቆይተው ራሳቸውን በአራት የወዳጅነት ጨዋታ መፈተሽ ችለዋል። በወዳጅነት ጨዋታ ክለቡ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያለ ጎል ሲቋጭ በፋሲል ከነማ 1ለ0 ሲሸነፍ የአዳማን ከ20 አመት በታች ቡድንን 4ለ1 እና የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን ተወላጅ ስብስብን 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል። ራሱን በዝግጅት እና በወዳጅነት ጨዋታ ሲያጠናክር የሰነበተው ክለቡ የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ጨዋታውን በአዲስ አበባ ስታዲየም መስከረም 29 ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከሜዳው ውጪ በመግጠም እንደሚጀምር መርሀግብሩ ያመላክታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...