መነሻ ገጽ ሀላባ ከተማ የክለቦች ዝግጅት | ሀላባ ከተማ
ሀላባ ከተማቅድመ ውድድር ዝግጅትዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ሀላባ ከተማ

አጋራ
አጋራ

ለ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ሀላባ ከተማ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ስር በመደልደል የውድድር ዘመኑን ማድረግ ከቻሉ ክለቦች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ሀላባ ከተማ ሊጉን ጠንቅቆ በሚያውቀው አሰልጣኝ በሽር አብደላ መሪነት ምድቡን በበላይነት ከማጠናቀቅ ባለፈ በአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ጋሞ ጨንቻን በመርታት የውድድር ዘመኑን በሁለት ዋንጫ በመፈፀም በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ በቅቷል።

 

 

ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያሳደገውን አሰልጣኝ በሽር አብደላን እንዳስቀጠለ ክለቡይፋ ቢያደርግም የኋላ ኋላ በተፈጠሩ የላይሰንስ ጉዳዮች የተነሳ በሀድያ ሆሳዕና አመቱን ያጠናቀቀው እና ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ሊጉ ሀላባን የመራውን አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን በመጨረሻም መሾሙን አበሰረ። አሰልጣኙን በሀላፊነት ከቀጠረ በኋላ በይበልጥ በክለቡ ከነበሩ ነበራች ይልቅ በአዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን ወደ ማጠናከሩ የገባው ክለቡ በሊጉ የልምድ ባለቤት የሆኑትን አማካዩ ፍሬው ሰለሞን (ጣቁሩ) እና የግራ መስመር ተከላካዩን ኪሩቤል ወንድሙን ከወልዋሎ ፣ የተከላካይ አማካዩ በሀይሉ ግርማ (ባባ) የመስመር አጥቂው ሽመክት ጉግሳን እና የመሐል ተከላካዩ ፀጋአብ ዮሐንስን ከምድረገነት ሽረ ፣ ከመቻል ጋር በአመቱ አጋማሽ የተለያየውን ተከላካዩ ነስረዲን ሐይሉ ፣ አጥቂው ናትናኤል ሰለሞንን ከነገሌ አርሲ ፣ አቡሽ ደርቤን ከሀድያ ሆሳዕና ፣ ከከፍተኛ ሊጉ ደብረብርሃን ከተማ አጥቂው ፍሰሀ ቶማስ እና የመስመር አጥቂው ሀይደር ሽኩርን እንዲሁም አጥቂው ሱራጅ ከድርን ከመንጌ ቤላሻንጉል ክለቡ ከሀገር ውስጥ ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት ሦስት አመታት ቆይታን ማድረግ የቻለው ጋናዊው የመሐል ካሌብ አማንክዋ ፣ በኢትዮጵያ ቡና እና የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በወልዋሎ ያሳለፈው ሌላኛው ጋናዊው አጥቂ ኮንኮኒ ሀፊዝን እንዲሁም የቤኒን ዜግነት ያለውን ግብ ጠባቂ ራያን ሊሳሲን ኮተን ስፖርት ሴኔጋላዊውን አማካይ ሳምባ ሴክኝ ከዩኤስኤ አካም ክለቡ በይፋ ያስፈረማቸው 11 አዳዲስ ተጫዋቾች ሲሆኑ በክለቡ የነበሩ እንደ ያሬድ መሐመድ ፣ ፀጋ ደርቤ ፣ ፋሲል አበባየው እና ዮናታን ብርሀነን ጨምሮ ወደ አስር የሚደርሱ ነባር ተጫዋቾችን ውላቸውን በማደስ ክለቡ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በይፋ ከነሐሴ 25/2018 ጀምሮ በክለቡ መቀመጫ ከተማ ሀላባ ቁሊቶ በይፋ እንደጀመረ ሀትሪክ ስፖርት ያገኝኘው መረጃ ይጠቁማል።

በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ እየመራ በጂም እና በሜዳ በቀን ሁለት ጊዜ ሲሰራ የቆየው ክለቡ በቅርቡ ደግሞ በቀን አንድ ጊዜ ልምምዱን በማድረግ ዝግጅቱን ቀጥሏል። እስከ አሁን በወዳጅነት ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕናን ገጥሞ 1ለ0 ሲያሸንፉ በነገሌ አርሲ ደግሞ 4ለ1 ከተሸነፉበት ጨዋታዎች ውጪ ተጨማሪ የወዳጅነት ጨዋታን ያላገኘው ክለቡ በቀጣዩ ሳምንት ዕርብ በሜዳው በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከወልዋሎ ጋር ከማድረጉ በፊት ተጨማሪ የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ ጥረት በማድረግ የሚገኝ ሲሆን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ግን ክለቡ እያገባደደ እንዳለ በመረጃዎቻችን ማረጋገጥ ችለናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...