ደረጄ አለሙ በይፋ ለሸገር ከተማ ፊርማውን አኑሯል።

በአሰልጣኝ ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅ የሚመራው ሸገር ከተማ በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ሲሰራ የቆየ ሲሆን የመጀመሪያ ጨዋታውን ኢትዮጵያ ቡናን በፕሪምየር ሊጉ ከማስተናገዱ በፊት ግብ ጠባቂው ደረጄ አለሙን አስፈርሟል።
የቀድሞው የዳሽን ቢራ ፣ ወልድያ ከተማ ፣ አዳማ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ አዲስአበባ ከተማ እና በከፍተኛ ሊጉ ደብረብርሃን ከተማ ቆይታን ያደረገው ባለ ልምዱ የግብ ዘብ በይፋ ለሸገር ከተማ ፊርማውን አኑሯል።
አስተያየት ይስጡ