አበባየሁ ሀጂሶ ወደ ቀድሞው ክለቡ ሊመለስ ተቃርቧል ብለን የነገርናችሁ ዜና ዛሬ በይፋ የአንድ አመት ውል በመፈረም አረጋገጠ።

ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን መገኛቸውን ካደረገ በኋላ ለዋናው ቡድን ለተከታታይ አምስት አመታት ግልጋሎትን ከሰጠ በኋላ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ ቆይታን ማድረግ የቻለው እና በጉዳት ለወራት ርቆ በመልካም ጤንነት ላይ መገኘቱን ተከትሎ ለሳምንታት ከወላይታ ድቻ ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅትን ሲሰራ የነበረው አማካዩ አበባየሁ ሀጂሶ ወደ ልጅነት ክለቡ ወላይታ ድቻ ሊመለስ ከጫፍ መድረሱን ገልፀን የነበረ ሲሆን በይፋ በአንድ አመት ውል ክለቡን ዛሬ ተቀላቅሏል።
አስተያየት ይስጡ