የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፓትሪክ ቪየራ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጠንካራ እና ትልልቅ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ እናውቃለን። ጨዋታው ከባድ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል ለዚህም መፍትሄ አለን” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለብዙ ዓመታት በገዛ ሜዳው ጨዋታ ሳያደርግ የቆየ በመኾኑ ጨዋታው ከባድ ሊኾን እንደሚችል ገልጸዋል።
አሠልጣኙ የምንጫወትበት ስታዲየም እና የመጫወቻ ሜዳው ጥራት ለእኛ እጅግ ምቹ በመኾኑ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ እንወስደዋለን ብለዋል።
ዋናው ዓላማችን ጨዋታውን ማሸነፍ እና ሶስቱን ነጥብ ማግኘት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ጨዋታውን የትኛውንም ፈተና ተቋቁመን ማሸነፍ እንደምንችል ማሳየት አለብን ሲሉም አክለዋል::
ተጋጣሚያቸውን አክብረው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ እና በመስመሮች መካከል ክፍት ቦታዎችን ለማግኘት በፈጣን የጨዋታ መንገድ እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።
ማላንግ ሳር በበኩሉ “እዚህ በመገኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል:: ያለፈው አልፏል። አሁን ስለ ቀጣዩ ጨዋታ ነው የምናስበው” ሲል ከሞዛምቢክ ጋር ስላደረጉት ጨዋታ ተጠይቆ ሀሳቡን አጋርቷል::
ከቡድን እጋሮቼ ጋር በመሆን በነገው ጨዋታ የተሻለ ነገር እናደርጋለን ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።
አስተያየት ይስጡ