የኢትዮጵያ ከ 17 ዓመት በታች ቡድን ቀይ ቀበሮዎቹ ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ላይ የሚገጥማቸውን ሀገራት በዛሬው ዕለት በታንዛኒያ ዳሬሰላም በተደረገው የዕጣ ማውጣት መርሀግብር ማወቅ ችሏል።

በምድብ ሁለት የተደለደለው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ ዩጋንዳ እና ቡሩንዲ ጋር የሚገናኝ ሲሆን ውድድሩም ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10/2019 በሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ይካሄዳል። ውድድሩን ከአንድ እስከ ሦስት በመሆን የሚያጠናቅቁ ሀገራት ለ 2027 አፍሪካ ዋንጫ የሚያልፉም ይሆናል።

የ ኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባለፈው አመት በአሰልጣኝ ብንጃሚን ዚመር መሪነት በሞሮኮ በደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ አይዘነጋም።
አስተያየት ይስጡ