ነብሮቹ የውጪ ዜጋ አጥቂ አስፈረሙ።

በአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ እየተመሩ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቀመጫ ከተማቸው እየሰሩ የሚገኙት እና የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸውን በሜዳቸው ከባህርዳር ከተማ ጋር የሚያደርጉት ሀድያ ሆሳዕናዎች ጋናዊውን አጥቂ ሳሙኤል ቦአቲንግን በአንድ አመት ውል አስፈርመዋል።
ለሀገሩ ክለቦች አሻንቲ ኮቶኮ እና ሳማርቴክስ እንዲሁም በባንግላዲሺቹ ራማቴጋንጂ እና ሞሀመዳን ቆይታን ካደረገ በኋላ ቀጣዩ ክለቡ ሀድያ ሆሳዕና ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ