ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ህዝብ ለኢትዮጵያ ስፖርት ልማት ከፍተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱን ገልጸው ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ይህ ስኬት በአፍሪካ መድረክም እንዲደገም ድጋፍ ያደረጉትን አካላትን ያመሰገኑት ርዕሰ መስተዳድሩ የሠራችሁት ሥራ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ብለዋል። የመንግስት ድጋፍም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል። በመድረኩ በተደረገው ድጋፍም 80 ሚሊዮን 4መቶ ሺ ብር መሰብሰብ ተችሏል።
ለክለቡ የሚደረገው ድጋፍ በባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በሚከፈተው የሂሳብ ቁጥር በኩል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል ።
በሽኝቱና በገቢ አሰባሰብ መርሐግብሩ ላይ የሲዳማ ክልል ም/ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ም/ርዕሰ መስተዳድርና የት/ት ቢሮ ኃላፊ አቶ በየነ ባራሳ፣ የክልልና የዞኖች የሥራ ኃላፊዎች ፣ባለሀብቶች ፣የተቋም የሥራ ኃላፊዎች ፣የሀገር ሽማግለዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
አስተያየት ይስጡ