መነሻ ገጽ አርባምንጭ ከተማ አርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ እና በበርካታ ተጫዋቾችን አስፈረመ
አርባምንጭ ከተማዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

አርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ እና በበርካታ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አጋራ
አጋራ

በቀጣዩ የ2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚካፈለው አርባምንጭ ከተማ 14 አዳዲስ እና የ8 ነባሮችን ፊርማ አግኝቷል።

ከ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በመውረዱ በቀጣዩ የ2019 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የሚካፈለው አርባምንጭ ከተማ ከአሰልጣኝ አዲሴ ካሳ ጋር እንደሚቀጥል የታወቀ ሲሆን ክለቡን በፍጥነት ወደ ሊጉ ለመመለስ በይበልጥ በአካባቢው ልጆች ላይ ያተኮረ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ የነባር ተጫዋቾችን ፊርማ እያገኘ ይገኛል። በዚህም መሠረት 14 አዳዲስ እና የ8 ነባሮችን ፊርማ አግኝቷል።

በካፋ ቡና ፣ ቡሌ ሆራ ፣ ሀዲያ ሌሞ ፣ እንጅባራ ከተማ ፣ ዱራሜ ከተማ እና አክሱም ከተማን ማሰልጠን የቻለው እና ዱራሜ ከተማን ወደ ከፍተኛ ሊጉ ያሳደገው አሰልጣኝ አዲሱ ዶይሳ (ወዲዴ) የአርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

ክለቡን የተቀላቀሉትን አዳዲስ ተጫዋቾን ስንመለከት ሁለገቡ የቀድሞው የጋሞ ጨንቻ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ንግድ ባንክ ተጫዋች አስጨናቂ ፀጋዬ ፣ በአርባምንጭ በአዳማ እና ንግድ ባንክ የተጫወተው ተከላካዩ መላኩ ኤልያስ ፣ ተከላካዩቹ ኩጋት ናትናኤል ከልማት ውድድር ፣ ታምራት ዮሴፍ ከኮንሶ ኒዮርክ ፣ ማቲዮስ ማዳልቾ ከጂንካ ከተማ ፍፁም አለማየሁ ከስልጤ ወራቤ ፣ አማካዮቹ ግርማዬ አስፋው ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ ይትባረክ በክሪ ከቡራዩ ከተማ ፣ ብርሀኑ ወልቅጦ ከባቱ ከተማ ፣ አማካዩ የርዳኖስ እያሱን ከቤንች ማጂ ቡና ፣ ሳሙኤል ተስፋዬ ከመልካ ኖኖ ፣ አያልቅበት በቀለ ከየካ ክፍለከተማ አጥቂዎቹ ዘካሪያስ ፍቅሬ ከሻሸመኔ ከተማ ፣ ብሩክ ገዛኸኝ ከተስፋ ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የተከላካዮቹን አሸናፊ ፊዳ እና አስቻለው ስሜ ፣ የግብ ጠባቂው ሰራዊቴ ሰያ ፣ አማካዩቹ መሪሁን መስቀሌ ፣ ቴዎድሮስ በንቲ ፣ ቴዎድሮስ አጬ ፣ አብነት አባይነህ ፣ አጥቂው ይድነቃቸው ያሲን እና በሀይሉ ተስፋዬ ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ተራዝሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...