መነሻ ገጽ ሀላባ ከነማ “እንዲያስተካክሉ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ጠይቄ ነበር ያንን አላደረጉልኝም” አሰልጣኝ በሽር አብደላ
ሀላባ ከነማዜናዎች

“እንዲያስተካክሉ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ጠይቄ ነበር ያንን አላደረጉልኝም” አሰልጣኝ በሽር አብደላ

አጋራ
አጋራ

“ከእኛ ጋር አልተለያየም ኤ ላይሰንስ ያለው አሰልጣኝ ስለሚያስፈልግ ነው የምንቀጥረው” አቶ ወዳጆ ሙንዲኖ

ወደ 2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካደጉ ሁለት ክለቦች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ሀላባ ከተማ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ካሳደገው አሰልጣኙ በሽር አብደላ ጋር በሊጉ ላይ እንደሚቀጥል ክለቡ ማሳወቁን ተከትሎ አሰልጣኙ ወደ ዝውውሩ ገብተው ተጫዋቾችን ማስፈረም ቢጀምሩም የኋላ ኋላ ግን ክለቡ በራሱ መንገድ ተጫዋቾችን እያስፈረመ መገኘቱን ተከትሎ ደስተኛ አደለሁም በሚል አሰልጣኝ በሽር አብደላ ለክለቡ ደብዳቤ እንዳስገቡ ለሀትሪክ ስፖርት ተናግረዋል።

“የለፉ እና ነባር ተጫዋቾች መገፋት የለባቸው የሚል ቅሬታ ነበረኝ ይህንንም እንዲያስተካክሉ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ጠይቄ ነበር ያንን አላደረጉልኝም ከ15 ወሳኝ ተጫዋቾች 6ቱ ተባረሩብኝ ተስተካክሎ ወደ ስራ መግባት እፈልጋለሁ ብላቸውም በራሳቸው ተጫዋቾችን አስፈረሙብኝ ያም እኔን ደስተኛ አላደረገኝም ስለመለያየቴም የደረሰኝ ደብዳቤ የለም።” ሲሉ አሰልጣኙ ነግረውናል። የአሰልጣኙን ጉዳይ ይዘን በጉዳዩ ላይ ሀሳብ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ወዳጆ ሙንዲኖ እንደገለፁልን “እኛ አልተለያየንም ሦስተኛ አሰልጣኝ ሆኖ ይቀጥላል ነው ያልነው እኛ አንለያይም መለያየትም ፍላጎት የለንም ግን ኤ ላይሰንስ ያለውን አሰልጣኝ እንቀጥራለን ገና አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠርም በንግግር ላይ ነን።” በማለት ከሀትሪክ ስፖርት ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል።

ክለቡ ቀጣዩን አሰልጣኝ ለማሳወቅ ፍቃደኛ ባይሆንም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ወልድያ ከተማ እና ያለፉትን ሁል አመታት ሀድያ ሆሳዕናን በረዳት እና የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት ያሳለፉትን አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድን ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ለመቅጠር ማሳቡን ሰምተናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...