ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከላካይ አስፈረመ
በአዳማ ከተማ በቀጣዮቹ ቀናት የቅድመ ውድድር ልምምዳቸውን የሚጀምሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ቡድናቸውን ማጠናከር ቀጥለውበታል የመሀል ተከላካዩን ቁመታሙን ጊት ጋት ኩትን በሁለት አመት ኮንትራት ውል አስፈርመዋል።
የቀድሞው የአዲስ አበባ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ በአሁኑ ስአት በአሜሪካ ቢገኝም በኦንላየን ፊርማ ለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሁለት አመት ኮንትራት እንደፈረመ ተጫዋቹ በስልክ ለሀትሪክ ስፖርት ተናግሯል ።
አስተያየት ይስጡ