መነሻ ገጽ ባህርዳር ከተማ ባህርዳር ከተማዎች ልምምድ ሊጀምሩ ነው
ባህርዳር ከተማዜናዎች

ባህርዳር ከተማዎች ልምምድ ሊጀምሩ ነው

አጋራ
አጋራ

ባህርዳር ከተማዎች ከፊታችን ዕሁድ ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

ባላቸው ውል ላይ ሁለት ተጨማሪ አመታትን በባህርዳር ከተማ ያራዘሙት አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ለቀጣዩ የውድድር ዘመን የአምስተኛ አመት ቆይታቸውን በክለቡ የሚያደርጉ ሲሆን በክረምቱ የዝውውር መስኮትም አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም እና የሚፈልጓቸው ደግሞ ውላቸው በማደስ ወደ ዝግጅት ሊገቡ መሆኑን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

እስከ አሁን ወደ አስር የሚደርሱ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማለትም ሽመልስ በቀለ ፣ አስራት ቶንጆ ፣ ዮዳሄ ዳዊት ፣ኬኔዲ ገብረፃዲቅ ፣ ኪቲካ ጅማ ፣ እንዳሻው እሸቴ ፣ ማስተዋል ጋቻፎ ፣ ሐይደር ሙደሲር እና ዩጋንዳዊውን አጥቂ ቻርለስ ሙሴጌን በአዲስ መልክ ወደ ስብስባቸው ያካተተው ቡድኑ የሴኔጋላዊውን የግብ ዘብ ፔፕ ሰይዶ ፣ በረከት ጥጋቡ ፣ ወንድወሰን በለጠ ፣ ወንድሜነህ ደረጀ ፣ ግርማ ዲሳሳ ፣ ፍፁም ፍትህአለሙ ፣ አደም አባስ ፣ ትንሳኤ አዲሱ እና ብሩክ ሰሙን ውል ደግሞ ለተጨማሪ አመት ማራዘም የቻሉ ሲሆን ለ2019 የውድድር ዘመን ከፊታችን ዕሁድ ነሀሴ 10/2018 ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በአዳማ ከተማ ለማድረግ ማቀዳቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...