ሲዳማ ቡና ተመሳሳይ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመሩት እና ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ መርሀግብር ልምምዳቸውን ከሰሞኑን የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች ከውብሸት ክፍሌ እና ኤፍሬም ታምራት በመቀጠል ሁለት የውጪ ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

የሴኔጋል ዜግነት ያለው የ33 አመት ግብ ጠባቂ ወደ ሲዳማ ቡና አምርቷል። 1 ሜትር ከ85 ሴንቲ ሜትር ርዝማኔ ያለው ቼክኢን ንዶዬ ለሀገሩ ክለቦች ሬኔሳንስ ፣ ጃራፍ እና ሶናኮስ እንዲሁም ደግሞ የተጠናቀቀው አመት ደግሞ በሌላኛው የሀገሩ ክለብ ካምብሪን በ25 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለው ሲሆን ቀጣዩ ማረፊያው ሲዳማ ቡና ሆኗል።
ዩጋንዳዊው የተከላካይ አማካይ ሌላኛው የሲዳማ ቡና ተጫዋች ሆኗል። በኬኒያ ተወልዶ ያደገው እና ለአስራ ሁለት ክለቦች መጫወት የቻለው ይህ የ33 አመቱ ካሊድ አውቾ ከታንዛኒያዎቹ ያንጋ አፍሪካ እና ሲንጋዳ ክለቦች በመቀጠል ቀጣዩ መዳረሻው ሲዳማ ቡና ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ