ቅዱስ ጊዮርጊስ የፊታችን ዕርብ አዲሱን አሰልጣኝ በይፋ ይሾማል
ለ2019 የውድድር ዘመን በዝውውሩ ላይ በንቃት መሳተፉን የቀጠለው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰርቪያዊውን አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊቲን ሚቾን ሹመት የፊታችን ዕርብ አመሻሽ በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ እንደሚሾም ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

የአልጄሪያውን ክለብ ኢ ኤስ ስቲፍ ጋር ከተለያዩ በኋላ ከአራት ወራት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከዚህ በፊት በሁለት አጋጣሚ ስኬታማ ላደረጉት ክለብ አማካሪ በመሆን ክለቡ ከነበረበት አስከፊ የውጤት ምዕራፍ ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጎን በመቆም በአማካሪነት ያገለገሉት አሰልጣኙ ከሰሞኑ ከአንዳንድ ጉዳዮች ጋር ከፈረሰኞቹ ጋር ላይቀጥሉ ይችላሉ የሚሉ መረጃዎች ቢወጡም በመጨረሻም የጠየቋቸው ሁሉ ምላሽ ማግኘታቸውን ተከትሎ የፊታችን ዕርብ አመሻሽ 11 ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል ከክለቡ ጋር ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት እና ስለ ቀጣይ ዕቅዳቸው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ያገኘነው መረጃ ይጡቀማል።
በተያያዘ መረጃ ከክለቡ ጋር ውል ያላቸው አምስት ተጫዋቾች ከክለቡ ጋር በስምምነት በሚለያዩበት ጉዳይ ዙሪያ ከትላንት ጀምሮ ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛል።
አስተያየት ይስጡ