ለወልዋሎ ፈርሞ የነበረው አጥቂ በመጨረሻም ንግድ ባንክ ማረፊያው ሆነ
ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ድረስ በሁለት አጋጣሚዎች መጫወት የቻለው እና በመቀጠልም ለጅማ አባጅፋር ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት አመታት ደግሞ በሀድያ ሆሳዕና ቆይታን ማድረግ የቻለው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ እዮብ አለማየሁ ከአንድ ሳምንት በፊት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን ለሚወክለው ወልዋሎ ለመጫወት ስምምነት የፈፀመ ቢሆንም በዛሬው ዕለት ግን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሁለት አመት ውልን ፈርሟል።
አስተያየት ይስጡ