አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞን በዋና አሰልጣኝነት ከሰሞኑ የቀጠረው ኢትዮጵያ መድን በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ በመግባት አራት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የጋናዊውን ተከላካይ ውል ደግሞ አድሷል።
አቡበከር ሻሚል ወደ መድን አምርቷል። የቀድሞው የኮልፌ አርባምንጭ ፣ አዳማ እና ድሬዳዋ ያሳለፈው አማካዩ ቀጣዩ ማረፊያው ኢትዮጵያ መድን ሆኗል።

በመሐል ወደ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከማምራቱ ውጪ በመቐለ 70 እንደርታ ረጅሙን ጊዜ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው አሸናፊ ሀፍቱ ፣ የቀድሞው የስልጤ ወራቤ ፣ ሀላባ ከተማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ደሴ ከተማ አማካይ ከማል ሀጂ ከንግድ ባንክ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በጅማ አባጅፋር እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ ያደረገው ገለታ ሐይሉ መድንን በዛሬው ዕለት መቀላቀል ችለዋል።
በተጨማሪም የጋናውን ካሬላ ዩናይትድን ለቆ በድሬዳዋ ከተማ የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በመድን ቆይታ ያደረገው ጋናዊው ተከላካይ እስማኤል አብዱል ጋኒዮ ውሉ ለተጨማሪ አመት በክለቡ ተራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ