ባህርዳር ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል
የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛውን ውል በዛሬው ዕለት ያራዘመው ባህርዳር ከተማ አመሻሹን ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በመቐለ 70 እንደርታ በተከታታይ አመታት ግልጋሎት የሰጠው አማካዩ ኬኔዲ ገብረፃዲቅ እና የቀድሞው የሀላባ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ደሴ ከተማ ግብ ጠባቂ በመሆን ያገለገለውን እንዳሻው እሸቴን በሁለት አመት ውል አስፈርመዋል።

ክለቡ ከሁለቱ አዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ የቀድሞው የአቃቂ ፣ ወልዋሎ ፣ መቻል እና ቤንች ማጂ ቡና እንዲሁም ያለፉትን ሁለት አመታት በባህርዳር ቆይታን ያደረገውን በአጥቂ እና አማካይ ቦታ የሚጫወተውን የብሩክ ሰሙን ውል አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ