ሀላባ ከተማዎች የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል።
በአሰልጣኝ በሽር አብደላ የሚመሩት ሀላባ ከተማዎች የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል። የቀድሞው የነቀምት ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እና የተጠናቀቀውን አመት ደግሞ በደብረብርሃን ከተማ ያሳለፈው ፍሰሀ ቶማስ የሊጉን አዲስ አዳጊ ሀላባ ከተማን በይፋ መለቀል ችሏል።
የግብ ጠባቂው አባቱ ጃርሶን ውል ከቀናት በፊት ያደሰው ክለቡ የቀድሞውን የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ደሴ ከተማ አጥቂ የነበረውን ፀጋ ደርቤን ውል ለተጨማሪ አመት ማደስም ችሏል።
አስተያየት ይስጡ