አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ በኢትዮጵያ መድን ላይቀጥሉ የሚችሉባቸው ምክንያቶች እንዳሉ መረጃ አግኝተናል።
ኢትዮጵያ መድን በቅርቡ አራት አሰልጣኞችን ካወዳደረ በኋላ በመጨረሻም የቀድሞው የመተሐራ እና ሀምበሪቾ ዱራሜ ዋና እንዲሁም ደግሞ በአዳማ ፣ ኤሌክትሪክ እና ወላይታ ድቻ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን የሰሩትን ደጉ ዱባሞን በዋና አሰልጣኝነት መሾሙ ይታወሳል።
ክለቡን እንደተቀላቀሉ የተነገረላቸው አሰልጣኝ ደጉ ዱባሞ ክለቡ እያሳየ በሚገኘው የዝውውር መቀዛቀዝ እና ተያያዥ ምክንያቶች የተነሳ በክለቡ የማየት ዕድላችን የጠበበ እንደሆነ ባደረኩት ማጣራት ለማወቅ ችያለሁ ይሁን እንጂ አሰልጣኙ ወደ ከፍተኛ ሊግ ክለብ ሊያመሩ የሚችሉበት ዕድሎችም እንዳሉ የመረጃ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል።
አስተያየት ይስጡ