ቡታቃ ሸመና ወደ ፋሲል ከነማ አምርቷል
የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊሱ ፋሲል ከነማ ዘግየት ብሎም ቢሆን ወደ ዝውውሩ በመግባት አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኝ ሲሆን ቀጣዩ አዲሱ ፈራሚ አማካዩ ቡታቃ ሸመና ሆኗል።
ከአርባምንጭ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በክለቡ ላለፉት አምስት አመታት ቆይታን ማድረግ የቻለው ይህ ተጫዋች ቀጣዩ መዳረሻው በሁለት አመት ውል ፋሲል ከነማ መሆኑን የሰበሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አስተያየት ይስጡ