የፋሲል ከነማ ረዳት ለመሆን ተቃርቦ የነበረው አንጋፋው ደጉ ደበበ ወደ አዳማ አመራ
ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘ በኋላ ለረጅም አመታት እግር ኳስን የተጫወተው እና በቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካዊ ጊዜዎችን ያሳለፈው አንጋፋው የመሐል ተከላካይ ደጉ ደበበ የቀድሞው አሰልጣኙ ፋሲል ተካልኝ ጥሪ ተቀብሎ የአዳማ ረዳት አሰልጣኝ ሆኗል።
ከረጅም አመታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቆይታው ከለቀቀ በኋላ በወላይታ ዲቻ የመጨረሻ የተጫዋችነት ዘመኑን ያገባደደው የዋልያዎቹ የቀድሞው አምበል ከአርባምንጭ ከተማ የቡድን መሪነቱ በኋላ በሀድያ ሆሳዕና ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ አመቱን ካጠናቀቀ በኋላ የአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ረዳት ሆኖ ለመሾም ቢቃረብምም በመጨረሻም ምርጫው አዳማ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ