ከሲዳማ ቡና የሊጉን ዋንጫ ያነሳው አማካይ ወደ ሀዋሳ ከተማ ማምራቱ ዕርግጥ ሆኗል።
በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች እስከ አሁን አራት አዳዲስ ተጫዋቾን ማስፈረም የቻሉ ሲሆን ከደቂቃዎች በኋላ አማካዩ ሬድዋን ናስር የስብስባቸው አካል ያደርጋሉ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች ያለፈለትን ሁለት የውድድር ዘመን ከሲዳማ ቡና ጋር ቆይታ በማድረግ የሊጉን ዋንጫ ከክለቡ ጋር ያሳካው ተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያው ሀዋሳ ከተማ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ