አዳማ ከተማ የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፀመ።
አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን በቅርቡ በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው አዳማ ከተማ በዛሬው ዕለት ሦስት ተጫዋቾችን በሁለት አመት ውል የግሉ ማድረጉን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።

ይሁን እንዳሻው ወደ አዳማ አምርቷል። ከመተሐራ ከተገኘ በኋላ በድሬዳዋ ከተማ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ላለፉት ሁለት አመታት በአርባምንጭ ከተማ ከቆየ በኋላ በመጨረሻም አዳማ ከተማ አምርቷል።
ጀሚል ያዕቆብ ወደ ቀደመ ክለቡ በድጋሚ ተመልሷል። የቀድሞው የጅማ አባቡና እና ጅማ አባጅፋር ፈጣኑ የመስመር ተከላካይ አዳማ ከተማን ለቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ካመራ ከሁለት አመት በኋላ በድጋሚ የቀደመው ክለቡን መቀላቀል ችሏል።
ሌላኛው ወደ ቀደመ ክለቡ የተመለሰው አጥቂው ቦና አሊ ነው። የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር ተጫዋች አዳማ ከተማን ለቆ በመቐለ 70 እንደርታ ካሳለፈው አንድ አመት በኋላ ተመልሶ አዳማ ከተማን መቀላቀል ችሏል።
አስተያየት ይስጡ