የመስመር ተከላካዩ እና አጥቂው ፀጋአብ ግዛው በትላንትናው ዕለት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለማምራት በሁለት አመት ውል ስምምነት ፈፅሞ ወደ ልጅነት ክለቡ ለመመለስ መስማማቱ ይታወሳል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን መነሻውን ያደረገው ፈጣኑ ተጫዋች ያለፉትን ሁለት አመታት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታን ያደረገ ሲሆን በክለቡም ያለው መታወቂያ ወይንም ቴሴራ የቢጫ በመሆኑ ወደየትኛው ክለብ ቀሪ የሁለት አመት ውል በሀድያ ሆሳዕና ስላለው ወደየትኛውም ክለብ ማምራት አይችልም ሲሉ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አባተ ተስፋዬ በስልክ ለሀትሪክ ስፖርት የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።

የስራ አስኪያጁን ሀሳብ በመቀበል ጉዳዩን ለማጣራት ለተጫዋቹ ደጋግመን ብንደውልም ስልክ ማንሳት ባለ መቻሉ ሀሳቡን ማካተት ሳንችል ቀርተናል።
አስተያየት ይስጡ