በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ከታዩ ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ሽመልስ በቀለ ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ደግሞ በግብፅ ሊግ ላሉ በርካታ ክለቦች በመጫወት አስደናቂ አመታትን ማሳለፍ ችሏል።

ከሁለት አመት በፊት ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ለመቻል እና እንዲሁም ደግሞ ለአሳደገው ክለብ ሀዋሳ ከተማ የሁለት አመት ኮንትራትን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመፈረም በይፋ መቀላቀል የቻለ ቢሆንም በክለቡ በተፈጠሩ ያለመግባባት የተነሳ ከሳምንታት በፊት ያስገባው የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀባይነት በማግኘቱ ከክለቡ ጋር በዛሬ ዕለት ቀሪ የአንድ አመት ውል እየቀረው መለያየቱን ሀትሪክ ስፖርት ከክለቡ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ