ሀድያ ሆሳዕና የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ።
አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝነት የሾመው ሀድያ ሆሳዕና የመጀመሪያ ተጫዋቹን በእጁ አስገብቷል። ቢኒያም ጌታቸው ደግሞ የክለቡ አዲሱ ተጫዋች ሆኗል።
የቀድሞው የሀምበሪቾ ዱራሜ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና እንዲሁም ፋሲል ከነማ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ስድስት ወራትን ብቻ በቆየበት ኢትዮጵያ ቡና ሰባት ጎሎችን በማስቆጠር አስደናቂ አቋሙን ማሳየት የቻለ ሲሆን ከቡናማዎቹ ጋር አብሮ የሰራውን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን ጥሪ ተከትሎ ማረፊያው ነብሮቹ ቤት ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ