ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የአማካዩን ውል ደግሞ አራዝመዋል።
የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪው ወላይታ ድቻ በዛሬው ዕለት የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር ሲፈጅም የአማካዩን ውል ደግሞ አድሷል።

ሴኔጋላዊው የመሐል ተከላካይ አዳማ ዋዴ የጦና ንቦቹን በሁለት አመት ተቀላቀለ። ቁመታሙ 1.94 ሜትር ቁመት ያለው ተጫዋቹ በሀገሩ ክለብ ሳክሬ ጅማሮውን አድርጎ ለቱርኩ ኡምራኒየስፖር እና በጆርጂያው ሎኮሞቲቭ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀገሩ ሴኔጋል ተመልሶ ለጉይዲያዋየ ፣ ለቀድሞ ክለቡ ሳክሬ እንዲሁም ለኤኤስሲ ጃራፍ ከተጫወተ በኋላ መዳረሻው ድቻ ሆኗል።
ሁለተኛው የክለቡ ፈራሚ ሁለገቡ ተጫዋች ሱለይማን ሀሚድ ነው። ከአሶሳ ከተማ ከተገኘ ለአዳማ ከተማ ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የተጠናቀቀው አመት በመቐለ 70 አንደርታ ከተጫወተ በኋላ ቀጣይ መዳረሻው የጦና ንቦቹ ቤት ሆኗል።
ክለቡ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የአማካዩን ኪዳኔ አሰፋን ውል አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ