ወልዋሎዎች እዮብ አለማየሁን የወልዋሎ የመጀመሪያ ፈራሚ አድርገዋል።
በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ የሚመሩት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያ ተጫዋችን በእጃቸው አስገብተዋል። የቢጫዎቹ የመጀመሪያ ፈራሚ ደግሞ የመስመር አጥቂው እዮብ አለማየሁ ሆኗል።

ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በዋናው ቡድን ጭምር በሁለት አጋጣሚዎች የተጫወተው የቀድሞው የጅማ አባጅፋር እና ሀዋሳ ከተማ ተጫዋች ላለፉት ሁለት አመታት ባሳለፈበት ሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኙ የነበሩት የግርማ ታደሠን ጥሪ ተቀብሎ ወልዋሎን መቀላቀል ችሏል።
ትላንት የወሳኙን ተከላካይ ነፃነት ገብረመድህንን ውል ያደሰው ክለቡ በዛሬው ዕለት ተጨማሪ ዝውውሮችን እንደሚፈፅም ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ