በረከት ወልዴ ወደ ቀድሞው ክለቡ ከአራት አመት በኋላ ተመልሷል።

በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የሚመሩት ወላይታ ድቻዎች የቀድሞው ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል። ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን በ2008 ያደገው እና በዋናው ክለብም ጭምር የተጫወተው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በረከት ወልዴ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና የነገሌ አርሲ ቆይታው በኋላ በይፋ በዛሬው ዕለት ወላይታ ድቻን በሁለት አመት ውል ተቀላቅሏል።
አስተያየት ይስጡ