አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን ለአዳማ ከተማ አሳልፈው የሰጡት ነብሮቹ አዲሱ አሰልጣኛቸው ታውቋል።
ከቀናቶች በፊት ከአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ጋር ስምምነት ቢፈፅሙም ወደ አዳማ ከተማ አሰልጣኙ በማምራታቸው አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ሲያጤኑ የነበሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች በዛሬው ዕለት በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የተለያዩትን አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በቦታው ሾሟል።

የቀድሞው የሀረር ቢራ ፣ ዳሽን ቢራ ፣ ምድረገነት ሽረ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ሆነው ያገለገሉት አሰልጣኙ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በሁለት አመት ውል ኢትዮጵያ ቡናን በመረከብ በክለቡ ቆይታን ማድረግ የቻሉ ሲሆን ቀሪ የአንድ አመት ከስድስት ወራት ውል እየቀራቸው በቅርቡ መለያየት የቻሉ ሲሆን በመጨረሻም በዛሬው ዕለት የሀድያ ሆሳዕና አዲሱ አለቃ ሆነው መሾማቸውን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ