መነሻ ገጽ ዜናዎች የኖርዊች ሲቲ ክለብ ተጫዋች አሊ አህመድ ከሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር አብሮ እንደሚሰራና ለክለቡ አለም አቀፍ እገዛ እንደሚያደረግ ገለፀ!
ዜናዎች

የኖርዊች ሲቲ ክለብ ተጫዋች አሊ አህመድ ከሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጋር አብሮ እንደሚሰራና ለክለቡ አለም አቀፍ እገዛ እንደሚያደረግ ገለፀ!

አጋራ
አጋራ

ትውልደ ኢትዮዽያዊው አሊ አህመድ በቀጣይ የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አለማቀፋዊ ጉዞውን እውን ለማድርግ የራሱን ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጿል።

 

ምስረታውን ካደረግ አጭር ጊዜን ያስቆጠረው የሸገር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም፣ ክለቡን  በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ፣በውጪው አለም የጨዋታ አጋጣሚዎችን ለመፍጠር እና ዘመናዊ የክለብ አደረጃጀት ተሞክሮን ለመውሰድ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣም ይጠበቃል።

የካናዳ ብሔራዊ ቡድን አባልና እና የኖርዊች ሲቲ ክለብ ተጫዋች አሊ አህመድ በዛሬው ዕለት የከተማው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ሀላፊነቱን ወስዷል።

አሊ የሸገር ከተማ ምልክት ያለበት የክብር ሽልማት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ በተገኙበት የተበረከተለት ሲሆን፣ ይህም ለከተማዋ እግር ኳስ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው እና የሸገር ከተማን እግር ኳስ ክለብ ዓለም አቀፋዊ ጉዞ እና የክለቡን የረጅም ጊዜ እቅድ እውን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...