በመቻል ረዘም ያለ ቆይታን ያደረገው የግራ መስመር ተከላካዩ ውሉ ተራዝሟል።
ያለፉትን ስድስት አመታት በመቻል ቤት እየተጫወተ የሚገኘው እና ክለቡንም አምበል በመሆን ጭምር ሲያገለግል የምናውቀው የግራ መስመር ተከላካዩ ዳዊት ማሞ ለተጨማሪ አመት በመቻል የሚያቆየውን የሁለት አመት ውል ያራዘመ አምስተኛው ተጫዋች ሆኗል።

ተጫዋቹ መቻልን ከመቀላቀሉ በፊት በደብረብርሀን ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ