የ2016 የከፍተኛ ሊጉ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ከኤሌክትሪክ ጋር ሊለያይ ነው።
በ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሆን መሸለሙን ተከትሎ ነገሌ አርሲን በመልቀቅ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቶ ያለፉትን ሁለት አመታት በክለቡ ቆይታን ያደረገው ግብ ጠባቂው አሸብር ተስፋዬ ቀሪ የአንድ አመት ውል እየቀረው ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ለመለያየት ከጫፍ ደርሷል።

ወደ ሌሎች የፕሪምየር ሊግ ክለቦች እንደሚያመራ የሚጠበቀው ቁመታሙ የግብ ዘብ በዚህም ሳምንት ከክለቡ ጋር በሚኖረው ንግግር እንደሚለያይ ይጠበቃል።
አስተያየት ይስጡ