የሀድያ ሆሳዕና ቦርድ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥርን ፈፅሟል።

የሀድያ ሆሳዕና ቦርድ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን የክለቡ ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ማረጋገጥ ችለናል። ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገለገሉት እና ዘንድሮ ክለቡን ከበርካታ ፈተናዎች ጋር በመታገል ለስኬት አብቅተው ያጠናቀቁት የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ፣ መቻል ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ጭምር ያገለገለው አሰልጣኙ በሁለት አመት ውል አዲሱ የሀድያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ማምሻውን ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ