በሴቶች የሴካፋ ዞን ቻምፒየንስ ሊግ ተወዳዳሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአራት ተጫዋቾችን ኮንትራት አራዘመ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግን ለዘጠኝ ያህል ጊዜ በማንሳት ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው ኢትዮጵያዊ ንግድ ባንክ ላለፉት አራት አመታት የሊጉ አሸናፊ በመሆኑ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ መካፈል የቻለ ሲሆን በአፍሪካ ቻምፒዮን ሊግ ላይ ደግሞ አንድ የተሳትፎ ታሪክ አለው። ዘንድሮም በተመሳሳይ በሴካፋ ዞን ለአምስተኛ ጊዜ የሚካፈለው ክለቡ የአራት ነባር ተጫዋቾችን ውል አድሷል።

ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከተገኘች በኋላ አዳማ ከተማ ላለፉት አራት አመታት ደግሞ በንግድ ባንክ የቆየችው የቀኝ ተከላካዩዋ ናርዶስ ጌትነት ፣ የቀድሞው የሲዳማ ቡና እና መቻል በዶምሩ በንግድ ባንክ በሁለት አጋጣሚ ሰባተኛ አመቷ ላይ የምትገኘው የግራ መስር ተከላካዩዋ ታሪኳ ዴቢሶ እና በአርባምንጭ እና ሀዋሳ አሳልፋ ባለፈው አመት ክለቡን መቀላቀል የቻለችው ትዕግስት አዳነ ሦስቱም በተመሳሳይ ለሁለት አመት እንዲሁም በሁለት አጋጣሚዎች ለክለቡ በድምሩ ለስድስት አመታት መጫወት የቻለው ሀሳቤ ሙሶ ለአንድ ተጨማሪ አመት ውላቸውን በክለቡ ሲያራዝሙ በቀጣይ የዝውውር ቀን መከፈትን ተከትሎ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ ሀገር አዳዲስ ተጫዋቾችን እንደሚያስፈርም መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አስተያየት ይስጡ