መነሻ ገጽ ወልዋሎ “የእነርሱ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነበር” አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ
ወልዋሎዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

“የእነርሱ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነበር” አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ

አጋራ
አጋራ

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ ውል ለማደስ ተስማሙ።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ማድረግ የቻሉት እና አመቱን በብዙ ውጣ ውረዶች ያሳለፉት አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት በወልዋሎ ለመቆየት ስለ መስማማታቸው ለሀትሪክ ስፖርት ተናግረዋል። በትውልድ ከተማቸው ክለብ ሀድያ ሆሳዕና የጀመሩት እና ለሁለት ጊዜያትም ያህል ክለቡን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደግ የቻሉት አሰልጣኙ ደቡብ ፓሊስም በተመሳሳይ ወደ ሊጉ ማሳደግ የቻሉ ሲሆን በከፍተኛ ሊጎቹ ስልጤ ወራቤ እና ሀምበሪቾ ዱራሜም ቆይታን አድርገዋል።

ወልዋሎን የጥሎ ማለፍ አሸናፊ በማድረጋቸው በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ክለቡን ተሳታፊ ያደረጉት አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ ውላቸው መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ከፋሲል ከነማ ጋር ንግግር በማድረጋቸው ወደ ክለቡ ያመራሉ ተብሎ ቢጠበቅም ትላንት አመሻሽ ከወልዋሎ ቦርድ ጋር ድንገት በተደረገ ውይይት የቀረበላቸው አማላይ ጥቅማጥቅም በክለቡ ለመቀጠል እንዲስማሙ እንዳደረጋቸው ይገልፃሉ። “የእነርሱ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነበር ትላንት አመሻሹን ከግማሽ ሰዓታት ከፈጀ ንግግር በኋላ በክለቡ ለሁለት አመት ለመቀጠል በቃል ደረጃ ተስማምቻለሁ የቀረበልኝ ጥቅማጥቅም በቀላሉ ሌላ ክለብ የማገኘው አይደለም” ሲሉ ሀሳባቸውን ለጣቢያችን ገልፀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...