መነሻ ገጽ ሸገር ከተማ የሸገር ከተማ ለታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክቶች የትጥቅ ድጋፍን አደረገ
ሸገር ከተማዜናዎች

የሸገር ከተማ ለታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክቶች የትጥቅ ድጋፍን አደረገ

አጋራ
አጋራ

የሸገር ከተማ አስተዳደር ለታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክት ሰልጣኞች ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የስፖርት ቁሳቁሶች ድጋፍን በዛሬው ዕለት አደረገ።

ስፖርት የአካል ብቃት መዳበርን ፣ አንድነት እና ወንድማማችነትን እንዲሁም ደግሞ ጥሩ የሀገር ገፅታን በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ፣  ይህም ስነ-ምግባር እና መልካም ባህሪን የተላበሰ ፣ በምርታማነት ላይ የድርሻውን የሚወጣ ትውልድ ለማፍራት በእጅጉ ያስችላል።

መንግስት ይህንን በመረዳት በስፖርት ልማት እና ዕድገት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን ፣ ይህንንም ስኬታማ ለማድረግ የአቅም እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናዎችን በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች በየጊዜው እየሰጠ ይገኛል።

ሸገር ከተማም ከአመሰራረቱ አንስቶ ለታዳጊ የስፖርት ስልጠና መርሃ-ግብር ልዩ ትኩረትን በመስጠት ፣ አርዐያ የሚሆኑ ጠንካራ ቡድኖችን በማፍራት የከተማዋን አልፎም የሀገርን ስም የሚያስጠሩ ተተኪ ስፖርተኞችን  ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የከተማው ወጣቶች እና ስፖርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ናስር ሁሴን ገልፀዋል።

በከተማዋ በ12ቱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶች በሸገር ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት ዛሬ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለክረምት የስፖርት ስልጠናም ለ9 ሺህ 200 ስፖርተኞች ለ324 አሰልጣኞች በ18 የስፖርት አይነቶች የሚሰጥ ሲሆን ፣ ከዛሬ ጀምሮም ስልጠናው መሰጠት መጀመሩ ተገልጿል።

በተጨማሪም ለከተማው 5 የሞዴል ፕሮጀክቶች የስፖርት ትጥቆችን ጨምሮ እንደ እግር ኳስ ፣ መረብ ኳስ ፣ ቅርጫት ኳስ ፣ የባድመንተን ፣ ራኬት እና ሸትሊ  ያሉ ልዩ ልዩ የስፖርት ዕቃዎች በአጠቃላይ ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የስፖርት ትጥቆች እና  ቁሳቁሶች እንደተሰጠ አቶ ናስር ሁሴን ጨምረው አብራርተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...