ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀሪ ኮንትራት የነበራቸው አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር አይቀጥሉም።

ኢትዮጵያ ቡናን ከአሰልጣኝ አብይ ካሳሁን መሰናበት በኋላ የተረከቡት አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ቀሪ የአንድ አመት ከስድስት ወራት ውል እየቀራቸው ከቡናማዎቹ ጋር መለያየት ችለዋል።
የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በ51 ነጥቦች 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የውድድር ዘመኑን መቋጨት የቻለው ኢትዮጵያ ቡና በቀጣዩ ቀናት አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር መቃረቡን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ