መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ በጣሊያን ሴሪ ኤ የደመቀው ኮከቡ ግብ ጠባቂ
ኢትዮጵያን በውጪዋልያዎቹዜናዎች

በጣሊያን ሴሪ ኤ የደመቀው ኮከቡ ግብ ጠባቂ

አጋራ
አጋራ

ጣሊያኖች ጂያንሉጂ ዶናሩማን ይተካል ብለው ተስፋ የጣሉበት የሴሪአ አው ክለብ ካግሊያሪ ከኢትዮጵያዊ እናት የተገኘው ግብ ጠባቂ ማነው ?

እናቱ ኢትዮጵያዊት ስትሆን ስሟም ኤልሳቤት መላኩ ይባላል አባቱ ደግሞ ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው ሲሆን አሁን የምነግራችሁ ግብ ጠባቂ ደግሞ ከሁለቱ አብራክ በጣሊያኗ ቬሮና ከተማ ውስጥ ነው የተወለደው ፣ አንድ ሜትር ከዘጠና አንድ ሴንቲ ሜትር ርዝማኔ ያለው ኤልያና ካፕሪሌ። በአሁኑ ሰዓት ዕድሜው 24 የሞላው እና እግር ኳስን በጣሊያኑ ቼቮ አካዳሚ ውስጥ መጀመር የቻለ ሲሆን ወደ እንግሊዝም በማምራት በሊድስ ዩናይትድ ከ23 አመት በታች ቡድንም ውስጥ በመጫወት ድንቅ ጊዜን አሳልፏል። በመቀጠል ወደ ጣሊያን በመመለስ ለፕሮ ፓትሪያ ወጣት ቡድን ከተጫወተ በኋላ በጣሊያን ሁለተኛ ሊግ በሚሳተፈው ባሪ ክለብ ጥሩ ቆይታን በማድረጉ አቅሙን ከፍ እያደረገ መጥቶ በጣሊያን ምድር ከሚነሱ ስመ ጥር ግብ ጠባቂዎች ተርታ መመደብም ጭምር ችሏል።

በመቀጠል ወደ ትልቁ የጣሊያን ሊግ ሴሪ ኤ ከፍ በማለት ለታላቁ ናፓሊ በሁለት አጋጣሚዎች እንዲሁም በኢምፖሊም መለና ግልጋሎት በመስጠት ጥሩ ጊዜን ካሳለፈ በኋላ ባለፈው የ2025/26 የክረምት ዝውውር ወደ ሌላኛው የጣሊያን ሴሪ ኤው ክለብ ካግሊያሪ አቅንቶ ዘንድሮ ኢንተር ሚላን ቻምፒዮን በሆነበት አመት የኤሊያ ካፕሪሌው ክለብ የሆነው ካግሊያሪም 14ኛ ደረጃን በመያዝ አመቱን ማጠናቀቅ ችሏል። በሴሪ ኤው ለክለቡ 38 ጨዋታዎችን አድርጎ 53 ጎሎችን ያስተናገደው ይህ ግብ ጠባቂ ለጣሊያን ከ18 እና ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጠርቶ መጫወት ቢችልም በጅናሮ ጋቱሶው የአሰልጣኝነት ዘመን ለዋናው የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም የነጥብ ጨዋታን ተሰልፎ ማድረግ ሳይችልም ቀርቷል።

በወዳጅነትም ይሁን በነጥብ ጨዋታዎች ተሰልፎ ባለመጫወቱ ምክንያት በቀጣይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቢመረጥ የመጫወት ሰፊ ዕድል ያለው እና በቀጣዮቹ አመታት የወቅቱ የማንችስተር ሲቲን ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናርማን ተክቶ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ቋሚ የግብ ዘብ ይሆናል ተብሎ በቀድሞው ዝነኛ ግብ ጠባቂ ጂያሉጂ ቡፎን ጭምር የተመሠከረለት ተጫዋቹ ለጣሊያን ወይንስ ለኢትዮጵያ ይጫወታል የሚሉ ጉዳይ ቢጠበቁም ጣሊያንን የመምረጡ ነገር ሰፊ ስለ መሆኑ መረጃዎችን መመልከት ችያለሁ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...