በጣሊያን የሚገኘው ወጣቱ የቀኝ መስመር አጥቂ።

እግር ኳስ ተጫዋቾችን በማውጣት ከማትታማው የሀላባ ምድር መነሻው ቢሆንም በይበልጥ ወደ ጣሊያን ካመራ በኋላ ግን በእግር ኳሱ ከፍ ያለ ስምን ማግኘት እንደቻለ ይናገራል እንድሪስ ስክራሜሊ በአሁኑ ሰዓት 19 አመቱ ላይ የሚገኘው እንድሪስ በጣሊያኑ ዩዲኒዜ ወጣት ቡድን መነሻውን ያደረገ ሲሆን የክለቡ ከ17 እና ከ19 አመት በታች ቡድኖች ውስጥም ራሱን በደንብ ማብቃት ችሏል።

በቀኝ መስመር አጥቂነት የሚጫወተው እና በአሁኑ ሰዓት በጣሊያን ከ20 አመት በታች ቡድን ውስጥ የሚገኘው ይህ ወጣት ከጣሊያን ሴሪያ ወርዶ በሁለተኛው ሴሪ ቢ ሊያድግ የተቃረበ ሲሆን እንዲህ ሲልም ተደምጧል። ወደፊት ይላል አላህ ካገዘኝ ለተወለድኩባት ሀገር መጫወትን በደንብ እፈልጋለሁ ሲል ተደምጧል።
አስተያየት ይስጡ