መነሻ ገጽ ዜናዎች አበረታች ቅመሞችን በመከላከል የጋዜጠኞች ሚና በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
ዜናዎችፀረ-አበረታች ቅመሞች

አበረታች ቅመሞችን በመከላከል የጋዜጠኞች ሚና በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ጋር በመተባበር በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ እና በጋዜጠኞች የዘገባ ስነ-ምግባር ላይ ያተኮረ ውይይት በአዳማ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ መክፈቻ ላይ
ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት አምስት እና ስድስት ዓመታት የሀገሪቱን ስፖርት ከነበረበት የዶፒንግ ስጋት ለመታደግ እና ጠንካራ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት ህብረተሰቡ ዶፒንግን እንዲጸየፍ እና ንጹህ የስፖርት ማህበረሰብ እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የሚዲያ ባለሙያዎች ያበረከቱት አስተዋጽዖ ከፍተኛ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰው ሃይል፣ በአደረጃጀት፣ በአሰራር እና በግብዓት ራሱን በማጠናከር በአፍሪካ ደረጃ ተምሳሌት መሆን የሚችል ጠንካራ ተቋም መቋቋም መቻሉም ዋና ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

የአበረታች ቅመሞችን መከላከል ትምህርትን በሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ማስገባት መቻሉ፣ ወደፊት ወደ ስፖርቱ የሚቀላቀሉ ዜጎች በቂ እውቀትና ስነ-ምግባር እንዲኖራቸው ለማድረግ ባለስልጠን መስሪያ ቤቱ መስራቱንም በመልዕክቱ ተካቷል። ​የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴን ማጠናከር ያስፈለገበትን ምክንያቶች ዋና ዳይሬክተሩ በአራት ዋና አላማዎች ከፍለው አብራርተዋል። የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል እና በዓለም አቀፍ መድረክ ውጤታማ ሆኖ ለመቀጠል ዶፒንግን ያለመታከት መከላከል እንደሚገባ፤ ካልሆነ ግን ውድድሩ የሳይንቲስቶችና የቴክኖሎጂ ባለቤቶች ብቻ ይሆናል ብለዋል።

በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ በዶፒንግ ዙሪያ የተቀመጡ ጥብቅ መስፈርቶችን ማሟላት ሲቻል ሁለተኛው ጉዳይ ሲሆን ውድድሮችና ስልጠናዎች ያለምንም አበረታች ቅመም፣ በተፈጥሯዊ ተሰጥኦ እና በሳይንሳዊ ልምምድ ላይ ብቻ የተመሰረቱ እንዲሆኑ በሶስተኛ ደረጃ ተቀምጧል። በሌላ መልኩ የስፖርትን ተዓማኒነትና ውበት መጠበቅ ስፖርት ያለ ደጋፊ ምንም በመሆኑ፣ ደጋፊው ደግሞ ንጹህ ውድድርን ስለሚሻ፤ የስፖርቱን ተዓማኒነት ጠብቆ ደጋፊው ከሜዳ እንዳይጠፋ ለማድረግ እንደሆነ ተመላክቷል።

አበረታች ቅመሞች በዜጎቻችን ላይ የሚያስከትሉት የጤና፣ ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ዜጎቻችንን ከዚህ አደጋ የመጠበቅ እና የመከላከል ትልቅ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ ቢሆንም የሚዲያ ዘርፉ በዋናነት የላቀ ድረሻ እንዳለው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል። አክለውም የስፖርቱ ተዓማኒነት እንዲቀጥልና የስፖርት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት የጀመሩትን የተቀናጀ ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶፒንግ እና የጋዜጠኞች የዘገባ ስነምግባር፣ የአበረታች ቅመሞች ፅንሰ ሀሳቦች፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ የዶፒንግ ተፅዕኖ እና የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ በሚል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...