መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀደሙ ስፖንሰሮቹን ባገኘበት ጉባኤ ጊዜያዊ ቦርድም አቋቋመ
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅዱስ ጊዮርጊስ የቀደሙ ስፖንሰሮቹን ባገኘበት ጉባኤ ጊዜያዊ ቦርድም አቋቋመ

አጋራ
አጋራ

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በርካታ ደጋፊዎቹ በተገኙበት ታሪካዊ የተባለውን ስብሰባ በዛሬው ዕለት በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ አከናወነ።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜያዊ የቦርድ አባላቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣ መድረኩን በመሩት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ እና የቀድሞው ተጫዋቹ ሠለሞን መገርሳን ጨምሮ የአዲስአበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ሌሎች አመራሮች እና እንዲሁም የክለቡ በርካታ ደጋፊዎች በተገኙበት ፒያሳ በሚገኘው አድዋ ሙዚየም አዳራሽ በይፋ ለደጋፊው አሳውቋል። አስቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ንግግር ማድረግ የቻሉ ሲሆን ህዝባዊ የሆኑ ክለቦች መደገፍ ግዴታ መሆኑን እና ታሪካዊውን ክለብ ወደ ጠንካራ ተቋምም ማምጣት እንደሚገባም በንግግራቸው ጠቁመዋል።

ዛሬ የተመረጡት የቦርድ አካላት እስከ ጥቅምት 30/2019 ድረስ ብቻ ጊዜያዊ ሆነው የሚያገለግሉ ሲሆን በጥቅምት ወር በሚኖረው የክለቡ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ግን ለአራት አመታት ክለቡን በቋሚነት የቦርድ አባላቱን በምርጫ ሳይሆን በቀጥታ ምደባ እንደሚመረጥ አቶ ጀማል አህመድ ይፋ አድርገዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን ወደ ነበረበት ከፍታ ለመመለስ አልሞ በተከናወነው ጉባኤ ላይ ክለቡን ርቀው የነበሩ የቀድሞው ትልልቅ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች ወደ ክለቡ መመለሳቸው ይፋ የተደረገ ሲሆን ክለቡም የራሱ ዘመናዊ ስታዲየም እንዲኖረው የስታዲየሙን ዲዛይንም ለደጋፊዎቹ ይፋ ማድረግ የቻለ ሲሆን በቀጣይም በራሱ የሚቆም ጠንካራ ክለብ አድርጎ መገኘትም በከፍተኛ ሁኔታ በዕቅድ መያዙም ተገልጿል።

ክለቡ ጠንካራ የደጋፊ ማህበር እንዲኖረው እንደሚደረግ በዋናነት ደግሞ ከአሁን በኋላ ልክ እንደበፊቱ ቡድኑን የሚደግፉት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ፣ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ፣ ዳሽን ባንክ እና ሞሐ ለስላሳ (ፔፕሲ) ከፍተኛ ወጪ እያወጡ ክለቡን ስለሚደግፉ ገቢ እና ወጪውን በውስጥም ሆነ በውጪ ኦዲተር ማወቅ ስለሚኖርባቸው ስትራቴጂካዊ የኢኮኖሚ ፓርትነር በመሆን በቦርድ ውስጥ ቋሚ አባል ሆነው እንደሚካተቱም ይፋ ተደርጓል። በተጨማሪም በቦርድ ውስጥ ደጋፊው ፣ በቅርቡ የተቋቋመው የቀድሞው የክለቡ ተጫዋቾች ማህበርም ጭምር መቀመጫ እንደሚኖራቸው አቶ ጀማል መሐመድ ይፋ አድርገዋል። ይህ ቦርድም የክለቡን ስራ አስኪያጅ እና ከውጪ ገለልተኛ ኦዲተር የመሰየም ስልጣን ጭምር እንደሚኖረው አክለው ገልፀዋል።

ክለቡን በጊዜያዊ የቦርድ አባልነት ለማገልገል የተሰየሙትን ስንመለከት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህግ አማካሪ እና ሀላፊው አቶ ነሲቡ ጫኮ ፣ የቢጂአይ ኢትዮጵያ የኮርፖሬት እና የውጪ ግንኙነት ሀላፊ አቶ በሐይሉ አየለ ፣ የዳሽን ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዮሐንስ ሚሊዮን ፣ የሞሐ ለስላሳ (ፔፕሲ) የሴልስ እና ዲስክሪፕሽን ሀላፊው አቶ እዝራ ብርሀኔ ፣ የቀድሞው የክለቡ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ እንዲሁም ሌላኛው የቀድሞው ተጫዋች ሠለሞን መገርሳ ፣ የክለቡ ደጋፊ የሆኑት የቻምበር ማተሚያ ቤት ባለቤቱ አቶ ዳዊት አስፋው ቻምበር ማተሚያ ባለቤት ፣ እንደ አቶ ጀማል ንግግር ከሆነ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ክለቡን በጋራ አብሮ ሲደግፉ የነበሩት ባለሀብቱ ኢንተርፕርነር አቶ ሠለሞን ጥላሁን ፣ ኤክስፖርተር እና ኢንፖርተር እንዲሁም የያንጎ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሀላፊው ቶፊክ መሐመድ ያሲን ክለቡን ጊዜያዊ ሆነው የቦርድ ሰዎች ሆነዋል።

በመጨረሻ ሌሎች ውይይቶች እና ደጋፊዎችም የተሰማቸውን ከገለፁ በኋላ ረፋዱን የነበረው ውይይት መቋጫውን አግኝቷል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...