መነሻ ገጽ ወላይታ ድቻ “የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

አጋራ
አጋራ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ ጨዋታ በወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን መካከል ተከናውኖ ጨዋታው ያለ ጎል ተጠናቋል። ከጨዋታው በላይ በርካቶች በእንባ ያራጨ አንድ ድርጊት በስታዲየሙ ተከስቷል። 98ኛው ደቂቃ ላይ የወላይታ ድቻው የመስመር እና የፊት መስመር አጥቂው ቅዱስ ቂርቆስ በመድን ሦስተኛው የሜዳ ክፍል ላይ ከጋናዊው ተከላካይ እስማኤል አብዱልጋኒዮ ጋር ግጭትን አስተናግዶ በርካቶችን በእንባ ያራጨ አሰቃቂ ጉዳት ተጫዋቹ በማስተናገዱ ለህክምና አዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ ወደሚገኘው ቤተዛታ ሆስፒታል በማምራት ለተጫዋቾቹ ድንገተኛ ክፍል የማገገሚያ ህክምና ከተደረገለት በኋላ ዛሬ ማምሻው የክለቡ ቡድን መሪ ግዛቸው ጌታቸው እና የቡድኑ የህክምና ቡድን ተጫዋቹን ለተጨማሪ ህክምና ወደ ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ይዘውት እያመሩ እንደሆነ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ ዝርዝር መረጃውን አድርሰውኛል።

እንደ ስራ አስኪያጁ ገለፃ ከሆነ የቀኝ እግሩ ከቁርጭምጭሚቱ በታች በህክምና አጠራር (dislocation) የተባለ ስብራትን ማስተናገዱን እና ቁርጭምጭሚቱ በላይ ያለች አንድ አጥንትም በተመሳሳይ ስብራት እንደገጠመው ገልፀው ቤተዛታ ሆስፒታል ለቀዶ ጥገናው ብቁ ባለመሆናቸው ለተጫዋቾቹ በፃፉት የሪፈር ደብዳቤ የወላይታ ድቻ መቀመጫ በሆነችው ከተማ በሚገኘው ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል እንዳመራ እና ተጫዋቾቹ በቦታው ሲደርስ የቀዶ ጥገና ኦፕሬሽን እንደሚሰራለት አቶ ምትኩ ያደረሱኝ መረጃ አመላክቷል። ተጫዋቹም ከሚደረግለት ህክምና በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ የአንድ አመት ጊዜን እንደሚፈጅበት በመረጃዬ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።

በ2016 ከወላይታ ድቻ ከ20 አመት በታች ቡድን በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ አማካኝነት ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ተጫዋቹ ተስፋ የተጣለበት እና ለወላይታ ድቻ ትልቅ አበርክቶን እያደረገ ይገኛል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...