መነሻ ገጽ ዜናዎች ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

አጋራ
አጋራ

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ ተጠባቂው ጨዋታም በመቻል የበላይነት ሲቋጭ ምድረገነት ሽረም ወሳኝ ድልን ተቀናጅቷል።

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ሀድያ ሆሳዕናን ባስተናገደበት የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተመጣጣኝ በሁለተኛው አጋማሽ ሲዳማ ቡና የተሻለ ቢሆንም የማሸነፍ በለሱ የቀናቸው ግን የአሰልጣኝ ካሊድ መሐመዱ ሀድያ ሆሳዕናዎች ናቸው። 62ኛው ደቂቃ ከራሳቸው ሜዳ በረጅሙ ያሻገሩትን ኳስ ተቀይሮ በሲዳማ ቡና በኩል የገባው መላኩ ከበደ ወደኋላ ገጭቶ ደስታ ደሙ በአግባቡ ያላራቀውን ኳስ ደስታ ዋሚሾ ከሳጥን ውጪ አክርሮ መቶ የመስፍን ሙዜ የጊዜ አጠባበቅ ስህተት ታክሎ ነብሮቹ አሸናፊ የሆኑበትን ጎል አግኝተው 1ለ0 መጠናቀቅ ችሏል። የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡናም ተከታታይ ሦስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ላይ ምድረገነት ሽረን ከኢትዮጵያ ቡና ያገናኘው ጨዋታ ከሸገር ደርቢ በኋላ ማሸነፍ ያልቻለው ኢትዮጵያ ቡና 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። የጠራ አጋጣሚን ከጎሉ በፊት የፈጠረው አቤል እንዳለ 12ኛው ደቂቃ ከእጅ ውርወራ አቤል ብርሀነ አሻምቶ ፉዓድ ኢብራሂም ከራሱ የግብ ክልል ማራቅ ያልቻለውን ኳስ አቤል እንዳለ ከሳጥን ጠርዝ አክርሮ መቶ የቀድሞው ክለቡ መረቡ ላይ በማሳረፍ ከወራጅ ስጋት ለመውጣት ለሚጣጣረው ምድረገነት ሽረ ወሳኝ ድልን አስገኝቷል።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ከወላይታ ድቻ በበርካታ ደጋፊዎች ፊት ያገናኘው ጨዋታ ጎል ሳይቆጠርበት 0ለ0 ተጠናቋል።

በሳምንቱ ተጠባቂ በነበረው እና በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የነበሩት መቻል እና ነገሌ አርሲን ያገናኘው መርሀግብር በአራት ጎል ፌሽታ መቻልን አሸናፊ ያደረገ ውጤት ተመዝግቧል። 8ኛው ደቂቃ ላይ ከግራ የተነሳች ኳስን ኮሊንስ ኮፊ በጥሩ ዕይታ ሰንጥቆ ሰቶት ቸርነት ጉግሳ ከግቡ የቀኝ ቋሚ ከጠበበ ቦታ ላይ ግብ በማስቆጠር ጦሩን መሪ አድርጓል። ከፍ ባለ ተነሳሽነት ጨዋታውን የቀጠሉት የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ልጆች አጋማሹ ሊገባደድ ሲቃረብ 45+3 የጭማሪ ደቂቃ ላይ ቸርነት ጉግሳ ላይ ርሆቦት ሰላሎ ሳጥን ውስጥ የሰራው ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ፈቱዲን ጀማል አስቆጥሮታል።

ከዕረፍት መልስመሰ ጨዋታውን ከቆሙበት የቀጠሉት መቻሎች 65ኛው ደቂቃ ከበረከት ደስታ ያገኘውን ኳስ ወደ ውስጥ ዳዊት ማሞ ሲሰጠው ቻርለስ ሙሴጌ ሦስተኛ ጎል ሲያደርግ 77ኛው ደቂቃ በረከት ደስታ ከቸርነት ጉግሳ የደረሰችውን ኳስ መረብ ላይ አስቀምጧች መቻሎች በጎል ተንበሽብሸው 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...