አሰልጣኙን ያሰናበተው መቐለ 70 እንደርታ ሌላ ሹመትን ፈፅሟል።

በያዝነዉ የዉድድር አመት ደካማ የዉድድር ጉዞን እያደረገ የሚገኘዉ መቐለ 70 እንደርታ ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ስንብት በኋላ የባለፈው አመት አሰልጣኙን ፀጋዬ ኪዳነማርያምን በሀላፊነት ቢሾሙምም አሰልጣኙ ባሳዩት ደካማ ጉዞ የተነሳ ከሀላፊነት ለማንሳት ተገዷል። ክለቡም አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ እንደሚቀጥር ቢጠበቅም አሰልጣኙ ፍቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ ምርጫውን የቀድሞው የሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ አሰልጣኝ የነበሩትን አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን የላይሰንስ ጉዳይ በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ የማያስችላቸው በመሆኑ በቴክኒክ አማካሪ ስያሜ ክለቡን መረከባቸው ታውቋል።
ዛሬ አመሻሽ ከተጫዋቾቹ ጋር ትውውቅ ያደረገው አሰልጣኙ ነገ መቐለ 70 እንደርታ ከ ኢትዮጲያ መድን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ሲሆን ክለቡን ለማትረፍም እስከ ዉድድር አመቱ መጨረሻ ቆይታን ያደርጋሉ።
አስተያየት ይስጡ